Food and Beverage

በቤ/ጉ/ክ/መ/የማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የካማሺ ዞን ማ/ቤቶች መምሪያ የምግብ ፍጆታ እና የወጥ ማጣፈጫ ዕቃዎችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር – : 001/2019/ዓ.ም

በቤ/ጉ/ክ/መ/የማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የካማሺ ዞን ማ/ቤቶች መምሪያ በህግ ጥላ ስር በሚገኙ የህግ ታራሚዎች ከጥቅምት 01/2019ዓ.ም እስከ ጥር 30/2019 ዓ.ም የአራት ወር /4/ ወር የምግብ ፍጆታ እና የወጥ ማጣፈጫ ዕቃዎችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

በዚህ መሠረት በሥራ ዘርፋ ፈቃድ አውጥታችሁ በሥራ ላይ የተሰማራችሁ ሁሉ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሰነዶችን መግዛትና መጫረት ተችላላችሁ።

1. የጨረታ ምዝገባ እና መክፈቻ ቦታ እዲሁም አቅርቦት በቤ/ጉ/ክ/መ/ ካማሺ ዞን በካማሺ አዳራሽ ይሆናል።

2. በተጠቀሰው የሥራ ዘርፍ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈለ።

3. የንግድ ፈቃድና የምስክር ወረቀት የዋናውንና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል የግብር መያ ቁር (TIN No) ያለው።

4 ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነና ከሚመለከተው የገቢዎች ባለሥልጣን መ/ቤት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።

5. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ካማሺ ዞን ማ/ቤቶች መምሪያ ቢሮ ቁጥር 12 ድረሰ በመምጣት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ከፍለው መሰድ ይችላሉ።

6. ተጫራቾች በምግብ ፍጆታየጨረታ ማስያዣ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው።

7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሠነድ ዝርዝር ስርዝ ድልዝ ያለበት ሆኖ ከተገኘ ተጫራቾቹ (ድርጅቱ) ወዲያውኑ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል።

8. በተቀመጠው የሰነደ ዝርዝር ላይ ከተራ ቁጥር 1፣2፣3፣5፤6፤7፤8፤9፤10፤13፤15፤19፤20፤እና 23 ላይ ያሉት የመኖ ቀለብ ናሙና ማቅርብ ይኖርባቸዋል።

9. ጨረታውን ላላሸነፉ ተጫራቾች (ድርጅቶች) መሥሪያ ቤቱ ያስያዙትን ሲፒኦ (CPO) ወዲያውኑ የሚመልስ ሲሆን የሸናፊው (ድርጅት)ሲፒኦ (CPO) ግን ከመ/ቤቱ ጋር በሚገባው ውል መሠረት ይያዛል።

10.ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱንና የውል ስምምነቱን በመውሰድ በመሙላትና በዝርዝር በማስቀመጥ ኦሪጅናል እና የማይመለስ ፎቶ ኮፒውን በመለየት በታሸገ ኤንቨሎፕ ወይም ፖስታ ውስጥ በማድረግ በዚሁ በተዘጋጀ በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን የጨረታው ማስታወቂያው 16ኛው ቀን ተጫረቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4:00 ላይ የሚከፈት ሲሆን ቅዳሜና የበዓል ቀናት ሲገጥም ወደ ሥራ ቀናት ይሻገራል።

11. ተጫራቾች የተጠቀሱትን የሰነዱ ዝርዝርት ላይ መ/ቤቶች 20% የመጨመርም የመቀነስ መብት አለው።

12. ተጫራቾች በጨረታው መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ባይገኙ የጨረታውን መክፈት ሂደት እያስተጓጉልም።

13. መ/ቤቱ አማራጭ ( የተሸለ) መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊም ሆነ በሙሉ የመመረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ : -- የካማሺ ዞን ማ/ቤቶች ድረሰ ቀርበው መረጃ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን 

በስልክ ቁጥር ፦ 09 13 43 58 13/ /09 17 44 48 95/ በመደወል ጠይቀው መረዳት ይችላሉ።

የቤ/ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት የማቤቶች ኮሚሽን
የካማሽ ዞን ማ/ቤቶች መምሪያ ካማሽ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-06
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ15 ተከታታይ ቀናት
  • Bid opening: 2026-10-07 10:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00
  • Region: Beneshangul Gumuz
  • Publishing entity: Kamash Zone Prisons Department
  • Bid bond: 10,000.00 (አስር ሺህ ብር)
  • Bid document price: 200.00 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 22, 2026)
  • Posted at: 2026-09-22T08:48:17.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders