Road and Bridge Construction
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ከተማና መሠረተ ልማት በ2019 በጀት ዓመት ከውስጥ ገቢ ከአስፓልት እስከ እስታድዬም መግብያ ድረስ የኮብል እስቶን እና ድች ግንባታ ሥራ በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብሔራዊ ከልላዊ መንግሥት የይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ከተማና መሠረተ ልማት በ2019 በጀት ዓመት ከውስጥ ገቢ ከአስፓልት እስከ እስታድዬም መግብያ ድረስ የኮብል እስቶን እና ድች ግንባታ ሥራ በጨሬታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት፡-
- ደረጃቸው GC/RC-5 የሆኑ ተጫራቾች በ2018 ዓ.ም የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ (ከሊራንስ ያላቸው) በክልል ወይም በፈደራል በክልሉ ንግድ ኢንዱስትሪ ቢሮ ወይም መምሪያ በአቅራቢነት የተመዘገቡ፤ህጋዊ ብቃት ያላቸው እና ማረጋገጫና ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ የጨረታ ማስከበሪያ /BlD Security/70000/ 50,000 /ሀምሳ ሺህ ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ መዘዣ(CPO ወይም Unconditional bank guarantee ማቅረብ ይኖርበታል።
- በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ ፕሮጀክቶችን ሠርቶ ለማስረከብ ከአሠሪ እና ከሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር ህጋዊ ውል ገብተው በሥራ ወቅት ከአሠሪ መስሪያ ቤት ወይም ከአማካሪ መስሪያ ቤት ማንኛውም ዓይነት የሥራ አፈፃፀም ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ሥራ ተቋራጮች የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም።
- በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በይርጋለም ከተማ በፕሮጀክቱም ሆኔ በመደበኛ በጄት ሥራ ውል ስምምነት ገብተው ሥራ ጀምረው ያላጠናቀቁ (ያልጨረሱ) ተቋራጮች ጨረታውን መግዛት ሆነ መወዳደር አይችሉም።
- በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ህጋዊ ፈቃዳቸውን ተ.ዕ.ታ (VAT) የተመዘገቡበትን ሰርተፍኬትና ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ20 (ሀያ) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 400 /አንድ መቶ ብር/ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቅ/ጽ/ቤት ብር በመክፈል ደረሰኛቸውን በመያዝ ይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ግዥ/ፋይናንስ ክፍል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ ።
- ተጫራቾቹ ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የግንባታ ሳይት በራሳቸው ወጪ አይተው ማረጋገጥ አለባቸው።
- የጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ የጨረታ ማስከበሪያ (bid bond/security) ፣ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ ሰነድ በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመፃፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 2:30 እስከ 5:30 ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ግዥ ፋይናንስ ክፍል ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ኦርጅናል ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 5፡30 ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8:30 ላይ ይከፈታል፣የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም።
- አሠሪው መ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አሸናፍው ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው መሠረት ለቅድመ ክፍያ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል ።
- የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል።
- በጨረታ አከፋፈት ስነ -ሥርኣት ላይ የተነበበው ዋጋ አርቴሜትክ ቼክ በሚደረግበት ጊዜ በሁለቱም መካከል ያለው ከ2%በላይ በታች ከሆነ ቀጥታ ከጨረታ ወጭ ይደረጋል ።
- የቀረበው ተክንካል ዶክመንት ኮፒው የማይታይ እና የማይነበብ ከሆኔ እንድሁም የምያጠራጥር ሁኔታ ብገኝ ኦርጅናሉን የማቅረብ ግዴታ አለበት።
- በጨረታ ላይ ያለው ጠቅላላ ዋጋ ከማንድስ ግምት /ከወቅቱ ከገቢያ ዋጋ 15% በላይ ከሆነ እና ከ 30% በታች ከቀረበ የወቅቱ የገቢያ መዋዠቅ እና የስራውን አገብጋቢነት በማስቀደም ከውድድር ውጭ ይደረጋል ።
- መ/ቤቱ የተሸለ አማራጭ ከገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆን በከፍል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የይርጋዓለም
ከተማ አስተዳደር ከተማና መሠረተ ልማት ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-12
- Bid closing time: 11:30
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ከቀኑ 5፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-12 14:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ከቀኑ 8:30 ሰዓት
- Region: Sidama
- Publishing entity: Sidama Zone Yirga Alem City Administration
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 400.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 22, 2026)
- Posted at: 2026-09-22T12:54:14.000Z
- Source: 2merkato