Road and Bridge Construction

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ከተማና መሠረተ ልማት በ2019 በጀት ዓመት ከውስጥ ገቢ ከእስፓልት እስከ ጉዱማል ፓርክ መግቢያ ድረስ የኮብል እስቶን እና ድች ግንባታ ሥራ በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ከተማና መሠረተ ልማት በ2019 በጀት ዓመት ከውስጥ ገቢ ከእስፓልት እስከ ጉዱማል ፓርክ መግቢያ ድረስ የኮብል እስቶን እና ድች ግንባታ ሥራ በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት -

  1. ደረጃቸው GC/RC-5 የሆኑ ተጫራቾች በ2018 ዓ.ም የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ (ክሊራንስ ያላቸው) በክልል ወይም በፌዴራል በክልሉ ንግድ ኢንዱስትሪ ቢሮ ወይም መምሪያ በአቅራቢነት የተመዘገቡ፣ ህጋዊ ብቃት ያላቸው እና ማረጋገጫና ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ የጨረታ ማስከበሪያ / BID Security/70,000 / 70,000 /ሳባ ሺህ ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም Unconditional bank guarantee ማቅረብ ይኖርበታል።
  2.  በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ ፕሮጀክቶችን ሠርቶ ለማስረከብ ከአሠሪ እና ከሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር ህጋዊ ውል ገብተው በሥራ ወቅት ከአሠሪ መስሪያ ቤት ወይም ከአማካሪ መስሪያ ቤት ማንኛውም ዓይነት የሥራ አፈፃፀም ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ሥራ ተቋራጮች የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም።
  3.  በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በይርጋዓለም ከተማ በፕሮጀክቱም ሆነ በመደበኛ በጀት ሥራ ውል ስምምነት ገብተው ሥራ ጀምረው ያላጠናቀቁ (ያልጨረሱ) ተቋራጮች ጨረታውን መግዛት ሆነ መወዳደር አይችሉም።
  4.  በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ህጋዊ ፈቃዳቸውን ተ.ዕ.ታ (VAT) የተመዘገቡበትን ሰርተፍኬትና ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ20 (ሀያ ) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 400 /አንድ መቶ ብር/ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቅ/ጽ/ ቤት ብር በመክፈል ደረሰኛቸውን በመያዝ ይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ግዥ ፋይናንስ ክፍል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
  5.  ተጫራቾቹ ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የግንባታ ሳይት በራሳቸው ወጪ አይተው ማረጋገጥ አለባቸው።
  6.  የጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ (bid bond/security) ፣ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናል እና ሀለት ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ ሰነድ በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመፃፍሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 2:30 እስከ 5:30 ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ግዥ/ፋይናንስ ክፍል ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ኦርጅናል ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት።
  7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 5፡30 ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8:30 ላይ ይከፈታል፣የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም።
  8. አሠሪው መ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9.  አሸናፊው ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው መሠረት ለቅድመ ክፍያ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል
  10. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል።
  11. በጨረታ አከፋፈት ስነ -ሥርዓት ላይ የተነበበው ዋጋ አርቴሜትክ ቼክ በሚደረግበት ጊዜ በሁለቱም መካከል ያለው ከ2%በላይ በታች ከሆነ ቀጥታ ከጨረታ ውጭ ይደረጋል
  12.  የቀረበው ቴክኒካል ዶክመንት ኮፒው የማይታይ እና የማይነበብ ከሆነ እንዲሁም የሚያጠራጥር ሁኔታ ቢገኝ ኦርጅናሉን የማቅረብ ግዴታ አለበት
  13. በጨረታ ላይ ያለው ጠቅላላ ዋጋ ከማንድስ ግምት ከወቅቱ ከገቢያ ዋጋ 15% /በታች ካቀረቡ የወቅቱ የገቢያ መዋዠቅ እና የሥራውን አገብጋቢነት በማስቀደም ብሬክ -ዳውን /Cost break dwon/ እንዲያቀርቡ ይደረጋል።
    • መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ከገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የይርጋዓለም ከተማ ፋ/ኢ/ልማት ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-12
  • Bid closing time: 11:30
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከቀኑ 5፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-12 14:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Region: Sidama
  • Publishing entity: Yirga Alem City FEDB
  • Bid bond: 70,000 ብር
  • Bid document price: 400.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 22, 2026)
  • Posted at: 2026-09-22T13:07:11.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders