Medical Equipment and Supplies
በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መስተዳድር የካፋ ዞን የገ/ፃዲቅ ሻዎ አጠቃላይ ሆስፒታል ለ2019 በጀት የኦክስጅን ማሽን መለዋወጫ እቃ ግዥ፣ የቧንቧ ዕቃዎች እና ህንፃ ተገጣጣሚ እቃ፣ ለተኝቶ ታካሚዎች የምግብ አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መስተዳድር የካፋ ዞን የገ/ፃዲቅ ሻዎ አጠቃላይ ሆስፒታል ለ2019 በጀት ዘመን ከዚህ በታች የተጠቀሱትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት
1 ሎት /1/ የኦክስጅን ማሽን መለዋወጫ እቃ ግዥ
2 . ሎት /2/ የቧንቧ ዕቃዎች እና ህንፃ ተገጣጣሚ እቃ ግዥ
3. ሎት /3/ ለተኝቶ ታካሚዎች የምግብ አገልግሎት ግዥ ብቻ ሲሆን ተወዳዳሪዎች የሚጠበቅባቸው ቅድመ ሁኔታዎች በሎት /3/ ቀደም ሲል በመ/ቤቱ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ያለው ተጫራች መወዳደር አይችልም በመቀጠል የገቢዎች ክሊራንስ ያለው
1. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ እና የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈሉ
2 . የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን ያላቸው እንዲሁም ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ
3. በመንግሥት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
4 . የእቃ አቅራቢነት ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ እና ለሎት /3/የገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ ግዴታ ነው
5. ተራ ቁጥር ከሎት/2/ ለወጡ ጨረታዎች ናሙና ማቅረብ መጫረት የሚችሉ መሆኑን ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ቦንጋ ገ/ፃ/ሻዎ/አ/ሆስፒታል 3ኛ ፎቅ ግዥ ንብረት አ/ር ቢሮ ቁ.22 በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር ለእያንዳንዱ ጨረታ /500/ አምስት ሞቶ ብር በመክፈል መውስድ ይችላሉ።
ለእያንዳንዱ ጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ሲፒኦ ወይም ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ቼክ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር አፍ ክሬዲት ማቅረብና ማስያዝ አለባቸው። የጨረታ ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ሰነድ በታሸገ ኢንቨሎፕ ዋጋ በመሙላት ቦንጋ ቦንጋ ገፃ ሻ/አ/አጠቃላይ ሆስፒታል 3ኛ ፎቅ ግዥና ንብረት አ/ር ቢሮ ቀ.22 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ላይ ፖስታዎችን ማስገባት ይችላሉ።
6. ጨረታው በ16ኛው ቀን ላይ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ቦንጋ ገ/ፃ/ሻ/አ/ ሆስፒታል 3ኛ ፎቅ ግዥና ንብረት አ/ር ቢሮ ቁ.22 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል።
7 . ተጫራች ያሸነፈበትን እቃ ሙሉ በሙሉ እስከ ቦንጋ ገ/ፃሻ አሆስፒታል ቅጥር ጊቢ በሚገኘው ግምጃቤት/ ንብረት ክፍል ለማቅረብ ፈቃደኛ የሆነ እና በበጀት ዘመኑ ተጨማሪ ግዥ ፍላጎት ሲቀርብ ባሸነፈ ዋጋ ማቅረብ የሚችል
8.ተጫራቾች ተሟልቶ አለመገኘት ሂደቱን አያስተጓጉልም።
9 . አሸናፊ ድርጅት ማሸነፉ ሲረጋገጥ ያሸነፈበትን የጠቅላላ ዋጋ 10% ውል ማስከበሪያ ለማስያዝ በሆሉ ስም በዝግ አካውንት ለማቅረብ ፈቃደኛ የሆነእና ማሸነፉ ከተረጋገጠበት አምስት ቀናት ቀርቦ የውል ስምምነት ለመፈፀም ፈቃደኛ የሆነ
10. ጨረታው የሚከፈተው ቦንጋ ገ/ፃሻ አጠሆስፒታል 3ኛ ፎቅ ግዥና ንብረት አ/ር ቢሮቁ. 22 ሲሆን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ የሚቀጥለው የሥራ ቀን ላይ ይሆናል።
ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ለበለጠ መረጃ
ስልክ ቁጥር 0473310316/047331236 ያገኙናል።
የገ/ፃ/ሻዎ/ አጠቃላይ ሆስፒታል / ከፋ ቦንጋ/
Tender details
- Deadline: 2026-10-09
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ላይ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-09 12:00
- Bid opening (note): ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ላይ 4፡30 ሰዓት
- Region: South West Ethiopia Region
- Publishing entity: Kafa Zone G/Tsadik Shawo General Hospital
- Bid bond: 50,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published on: Addis Zemen (Sep 24, 2026)
- Posted at: 2026-09-24T07:55:26.000Z
- Source: 2merkato