Building and Finishing Materials

የደ/ም/ኢ/ህ/ክ /መንግስት ካፋ ዞን ቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2019 ዓ/ም በጀት ዘመን ለስልጠና አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር 001/2019

የደ/ም/ኢ/ህ/ክ / መንግስት ካፋ ዞን ቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2019 ዓ/ም በጀት ዘመን ለስልጠና አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን ማለትም፤በሎት 1 የኮንስትራክሽን እቃዎች፤ በሎት 2 ሆቴልና ቱርዝም እቃ፣ በሎት 3 አግሮ ፕሮሰስንግ እቃ ፤ በሎት 4 አይሲቲ እቃዎች፤ በሎት 5 የጋርሜንት እቃዎች፤ በሎት 6 አውቶሞቲቪ እቃዎች፤ በሎት 7 ኤሌክትሪክ እቃዎች፤ በሎት 8 ሰርቤይንግ እቃዎች እና በሎት 9 እስቴሽኔሪ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ተወዳዳሪዎች፡-

1ኛ. በሙያ መስክ ወይም በዘርፉ የተመዘገቡና ለዘመኑ የታደሰንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው፣ ህጋዊ ዕቃ አቅራቢ ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይ ስለመሆናቸው እና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው።

2ኛ. የዕቃዎች ዝርዝር መግለጫ /specification/ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአ/አበባ መክሲኮ አከባቢ ከሚገኘው ተግባረእድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መግቢያ በር በአካል በመቅረብ በኮሌጁ የሂሳብ ቁጥር 1000029122877 ላይ የማይመለስ 300 ብር በማስገባት የመጫረቻ ሰነዱን መውሰድ ትችላላችሁ፡፡

3ኛ. ተጫራቾችጨረታው የሚታሸግበትና የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት የምጫረቱባቸውን እቃዎች በመለየት በአይነታቸው እያንዳንዱን የሚሸጡበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤምቬሎፕ ለየብቻ ዋናውና ኮፒውን በፖስታ በማሸግ የሚጫረቱበትን ዘርፍ የተጫራቾችን ስም ወይም ድርጅት በመፃፍና ማህተም በመምታት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በሰዓቱ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

4ኛ. የጨረታ ሳጥን የሚታሸገው የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት 16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አ/አበባ መክሲኮ አከባቢ ከሚገኘው ተግባረእድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መግቢያ በር ከረፋዱ 4፡00 ላይ ታሽጎ 4፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡ ሆኖም በጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ወቅት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪል ያለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አይከለከልም፡፡ እለቱ የእረፍት ወይም በዓል ቀን ከሆነ ወደ የሚቀጥለው ስራ ቀን ይተላለፋል፡፡

5ኛ. ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ፤ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተርኦፍ ክሬዲት ለያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማወዳደርያ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ቴክኒካል ሰነድ ውስጥ በማሸግ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በጨረታ የተሸነፉ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።

6ኛ. አሸናፊዎች ባሸነፉበት የዕቃ ዋጋ መጠን የውልማስከበሪያ 10% በባንክ የተረጋገጠ CPO፤ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተርኦፍ ክሬዲት ለያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማወዳደርያ ሰነድ ለየብቻ ማስያዝ እና ያሸነፉበትን የእቃ ናሙና ውል ከገቡበት 3/ሶስት/ ቀን ውስጥ ለኮሌጁ ቀድሞ ማቅረብ ይኖርባችዋል።

7ኛ. አሸናፊ ተጫራቾች ዕቃውን እስከ ቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ድረስ የትራንስፖርትና ማንኛውንም ወጪ በመቻል በውሉ ላይ በሚጠቀሰው ቀን ማቅረብና ማስረከብ አለባቸው፡፡ ለማያቀርቡት ለውል ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ አይመለስም፡፡

8ኛ. ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ከተከፈተበት እለት ጀምሮ ለ60 ቀናት ይሆናል።

9ኛ. በጨረታ ሰነዱ ላይ ማንኛውንም ማስተካከያ ማድረግም ሆነ ከቀረበው ሰነድ ውጭ መሙላት አይፈቀድም፡፡

10ኛ. ተጫራቾች ባሸነፉበት እቃ የካሽ ሪጅስቴር ደረሰኝ ከአታችሜንት ጋር አያይዞ ማቅረብ ወይም የካሽ ሪጅስቴር ደረሰኝ የማይጠቀሙ ከሆነ የማይጠቀሙበት ምክንያት ከገቢዎች መ/ቤት ደብዳቤ በማስደገፍ የእጅ በእጅ ደረሰኝ ጋር ማቅረብ አለባችሁ።

11ኛ. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0917 916 439 / 0913 466 023 / 0927 694 591 / ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት ካፋ ዞን ቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-09
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-09 12:00
  • Bid opening (note): ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: South West Ethiopia Region
  • Publishing entity: Bonga Poly Technic College
  • Bid bond: 10,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 24, 2026)
  • Posted at: 2026-09-24T08:01:32.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders