Poultry, Bee and Animal Husbandry
ኢትዮ ዌትላንድስና ናቹራል ሪሶርስ አሶሴሽን (EWNRA) ሀገር በቀል የልማት ድርጅት ሲሆን፤ ማህበረሰብ ተኮር ለሆነ የጋጣ ንብ ማንባት ሥራ አገልግሎት የሚዉል በቁጥር 3,658 (ሶስት ሺህ ስድስት መቶ ሃምሳ ስምንት) ኬንያ ቶፕ ባር ሞዴል የንብ ቀፎ በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
የንብ ቀፎ ሥራ ጨረታ ማስታወቂያ
ኢትዮ ዌትላንድስና ናቹራል ሪሶርስ አሶሴሽን (EWNRA) ሀገር በቀል የልማት ድርጅት ሲሆን፤ ማህበረሰብ ተኮር ለሆነ የጋጣ ንብ ማንባት ሥራ አገልግሎት የሚዉል በቁጥር 3,658 (ሶስት ሺህ ስድስት መቶ ሃምሳ ስምንት) ኬንያ ቶፕ ባር ሞዴል የንብ ቀፎ በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ስለዚህ በእንጨትና ብረታ ብረት ስራ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አካላት የጨረታዉን ሰነድ ከ ሰኞ, መስከረም 18/2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዓርብ, መስከረም 29 2019 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት አዲስ አበባ ከተማ ከሚገኘው ኢትዮ ዌትላንድስና ናቹራል ሪሶርስ አሶሴሽን (EWNRA) ዋና መስሪያ ቤት፣ ቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን-አማን ከተማ ከሚገኘው የፕሮጀክት ጽ/ቤት ወይም ኢሉ አባቦር ዞን መቱ ከተማ ከሚገኘው የፕሮጀክት ጽ/ቤት በመቅረብ በብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመግዛት መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን።
ተጫራቾች የጨረታዉን ሰነድ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማሸግ አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው ኢትዮ ዌትላንድስና ናቹራል ሪሶርስ አሶሴሽን (EWNRA) ዋና መስሪያ ቤት ለጨረታ ማስገቢያ ታስቦ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እንዲያስገቡ እናሳስባለን።
ጨረታው ሰኞ, ጥቅምት 02/2019 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡30 ይዘጋል። የጨረታው ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በተመሳሳይ ዕለት ማለትም ሰኞ, ጥቅምት 02/2019 ዓ.ም ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን።
ተጫራቾች በጨረታዉ ለመወዳደር መሟላት ያለባቸዉ መስፈርቶች (ቅድመ ሁኔታዎች)
- በእንጨትና ብረታብረት ስራ ለ 2018 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ የሙያ ፈቃድ ያለዉ
- የዘመኑን ግብር የከፈለ
- በንብ ቀፎ ስራ ህጋዊ እውቅና ካለው ገጠር ቴክኖሎጂ ማሰልጠኛ የሰለጠነና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- ካሁን በፊት ለሰራባቸዉ ተመሳሳይ ሥራዎች ማለትም ኬንያ ቶፕ ባር ሞዴል ባለፍሬም የንብ ቀፎ ስራ ከ3 በላይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት ተመዝጋቢ የሆነ
- የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታ ከገባበት ጠቅላላ ዋጋ መጠን 10% የሚሆን ሲፒኦ (CPO) በባንክ ማስያዝ የሚችል
- በድርጅቱ አቅራቢነት የሚገባውን የውል ስምምነት ህጎች የሚያከብር፤ ስራውን ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ውል ከተገባበት ቀን ጀምሮ ሁለት ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ሰርቶ የሚያስረክብ
- ጨረታውን አልፎ ወደ ውል ስምምነት የሚገባ ተጫራች ለቅድመ ክፍያ ዋስትና (Advance guarantee) የሚሆን ለሁለት ወራት ጸንቶ የሚቆይ ውል ከገባበት መጠን 30% የሚሆን የባንክ ዋስትና ደብዳቤ ወይም ሲፒኦ (CPO) ድርጅቱ በሚያስቀምጥለት የጊዜ ገደብ ውስጥ ማቅረብ/ማስያዝ የሚችል
ማሳሰቢያ
- የሚቀርበው የንብ ቀፎ ሥራ ዋጋ ከታች የተዘረዘሩት ከተሞች ድረስ የማጓጓዣ ዋጋን ታሳቢ ያደረገ መሆን አለበት ማለትም፡-
- 1,200 (አንድ ሺህ ሁለት መቶ) ቀፎ ሸካ ዞን ማሻ ከተማ ፣
- 400 (አራት መቶ) ቀፎ ካፋ ዞን ቢጣ ገነት ከተማ
- 2,058 (ሁለት ሺህ ሃምሳ ስምንት) ቀፎ ኢሉ አባቦር ዞን መቱ ከተማ
ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ አዲስ አበባ ከተማ ከሚገኘው ኢትዮ ዌትላንድስና ናቹራል ሪሶርስ አሶሴሽን (EWNRA) ዋና መስሪያ ቤት፣ ኢሉ አባቦር ዞን መቱ ከተማ ወይም ቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን ከተማ ከሚገኘው ድርጅታችን ፕሮጀክት ጽ/ቤቶች በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-552 7791/ 047-335 0634/ 047-335-0874 ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
ማሳሰቢያ
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነዉ።
Tender details
- Deadline: 2026-10-12
- Bid closing time: 14:30
- Bid opening: 2026-10-12 15:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethio Wetlands and Natural Resources Association
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: 2merkato.com (Sep 25, 2026)
- Posted at: 2026-09-25T10:05:35.000Z
- Source: 2merkato