Catering and Cafeteria Services
በንፋስ ስልከ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 02 አስተዳደር የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በንፋስ ስልከ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 02 አስተዳደር
- ሎት 1 የመስተንግዶ አገልግሎት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 2,340.00
- ሎት 2 የሠራተኞች መዝናኛ ክበብ አገልግሎት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,899.20
- ሎት 3 የትራንስፖርት አገልግሎት (ሕዝብ ትራንስፖርት የሚሰጡ መካከለኛ፣ የሕዝብ ትራንስፖርት አነስተኛ ሚኒባስና የጭነት አገልግሎት የሚሰጡ መኪናዎች) እና የጉልበት አገልግሎት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 6,407.20)
- ሎት 4 የጥገና አገልግሎት (የቢሮ የኤሌክትሮኒክስ ጥገናና የፈርኒቸር ጥገና) የፈርኒቸር ጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,580.00 እና የኤሌክትሮኒክስ ጥገና ጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,580.00
- ሎት 5 ህትመት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 806.70
- ሎት 6 ሞንታርቦና ዲኮሬሽን አገልግሎት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 2,703,60
- ሎት 7 ቋሚ ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 29,603.29
- ሎት 8 አላቂ የቢሮ እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 38,791.08
- ሎት 9 ደንብ ልብስ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 49,392.89
- ሎት 10 የፅዳት ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 63,489,67
በጨረታ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም የሥራ ዘመን የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶችን አላቂ የቢሮ እቃዎችን፣ የመስተንግዶ አገልግሎት እንዲሁም የቋሚ ዕቃዎች፣ ህትመት፣ ደንብ ልብስ፣ የትራንስፖርትና ጉልበት አገልግሎት፣ ሞንታርቦና ዲኮሬሽን አገልግሎትና የጥገና አገልግሎት ግዢዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
1. በመንግሥት ዕቃ አቅራቢነት ተመዝግቦ በፌዴራል ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የምስክር ወረቀት ያላቸው።
2. ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉና ንግድ ስም ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ የግብር ከፋይ ቲንና የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ከግብር ዕዳ ነፃ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸውእንዲሁም የሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ቫትን ጨምረው መሙላት አለባቸው።
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ በአንድ ሎት 300 ብር በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1 ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስር (10) የሥራ ቀናት ከዚህ በላይበተጠቀሰው የቢሮ ቁጥር በመምጣት መግዛት ይችላሉ።
5. በጨረታ ሰነድ ላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ናሙና ወይም ሳምፕል ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው። ናሙናና ሳምፕል ለማቅረብ የማይመቹ ዕቃዎችን በፎቶግራፍ እንዲሁም በካታሎግአጉልቶ በሚያሳይ መቅረብ አለባቸው።
6. አንዱ በሰጠው ዋጋ ላይ ሌላው ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም። በሥራ ዕድል ጽ/ቤት የተደራጁ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉት አምራች በሆኑበት ሥራ ዘርፍ ብቻ ነው።
7. ገዢው አካል የሚገዛውን ዕቃ እስከ ሃያ ፐርሰንት (20%) ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።
8. ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡትን ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በኤንቨሎፕ በማሸግ ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ ላይ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ከላይ በተዘረዘረው በየሎቱ መሠረት የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው። በተራ ቁጥር 4 በተጠቀሰው አድራሻ መሠረት ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ጨረታው እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይችላሉ።
9. አሸናፊው ከታወቀ በኋላ ለአሸናፊዎችና ተሸናፊዎች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለሳል።
10. አሸናፊ ተጫራቾች በሰነዱ ውስጥ በተመለከተው ጊዜ ገደብ ውስጥ ማለትም ማሸነፋቸው ከታወቀ ከሰባት ቀናት በኋላ ቀርበው በሰባት ቀናት ውስጥ የጠቅላላው ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% (አስር ፐርሰንት) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ አሠርተው ውል መዋዋል አለባቸው።
11. ጨረታው በአስረኛው ቀን ላይ ተዘግቶ በማግስቱ በአስራ አንደኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ቢሮ ቁጥር 1 አንደኛ ፎቅ ፋ/ጽ/ቤት ውስጥ ይከፈታል።
12. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- መካኒሳ አሚጎ ካፌ 500 ሜትር ከፍ ብሎ ብሎ በሚገኘው የንፋስ ስልክ ላፍቶ ወረዳ 02 አስተዳደር ቅጥር ግቢ ውስጥ
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0921547457/ 0918973904/ 0910256792/ 0910225112
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አስተደደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-07
- Bid closing time: 17:30
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስረኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ድረስ
- Bid opening: 2026-10-08 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Nifas Silk Lafto Sub City Woreda 02 FEDB
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር በየሎቱ
- Published on: Addis Zemen (Sep 26, 2026)
- Posted at: 2026-09-28T08:41:51.000Z
- Source: Qelal Tenders