Catering and Cafeteria Services

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስተዳደር የአራት ኪሎ ስፖርት፣ ትምህርትና ሥልጠና ማዕከል የምግብ ግብዓቶች ለአንድ ዓመት በአቅራቢነት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የምግብ ግብዓቶች ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 02/2019 ዓ.ም

በአራት ኪሎ ስፖርት፣ ትምህርትና ሥልጠና ማዕከል

1. የምግብ ግብዓቶች ለአንድ ዓመት በአቅራቢነት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የተጫራቾች መመረያ

በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች፡-

1, ለመጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የምግብ ግብዓት በሥራ መስከ፣ የዘመኑን ግብር፤ ለመክፈላቸውን ሕጋዊ በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

2. በመንግሥት የግዥ ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል Tin No ያላቸውና በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ አቅራቢነት ዝርዝርየተመዘገቡ እና ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርባቸዋል።

3. የዘመኑን ግብር የከፈሉበትና የቫት ተመዝጋቢ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

4. የዋጋ ማቅረቢያ ሲሞላ ስርዝ ድልዝ እንዲኖር አይፈለግም። ሰነዱ ስርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታው ውጪ ይሆናል።

5. ተጫራቾች በሙሉም ሆነ በከፊል ጨረታውን ተወዳድረው ካሸነፉና ከተዋዋሉ በኋላ ያሸነፉበትን ዕቃ በተሰጠው ለአንድ ዓመት ለማቅረብ ፈቃደኛ የሆነ ካልሆነ በውሉ መሠረት በሕግ ይጠየቃል። ለምግብ ግብዓት ባሸነፈው የዋጋ ጭማሪ ካለ ለሦስት ወር ከአቀረቡ በኋላ ከሀገሪቱ ገበያ ዋጋ ጋር ግምት ውስጥ ገብቶ ተነፃፅሮ ዋጋ ይሻሻላል።

6. ተጫራቾች መ/ቤቱ ያዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የምግብ ዝርዝር የያዘው የአንዱ ዋጋ ከነቫት መሙላት ይኖርባቸዋል። ዋጋ ሲሞላ የተጫራቹ ሙሉ ስም፣ ፊርማ፣ ማህተም ያረፈበት አድራሻ፣ ክፍለ ከተማ የቤት ቁጥርና የስልክ ቁጥራቸውን መግለፅ ይኖርባቸዋል።

7. ተጫራቾች መ/ቤቱ ያዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከአራት ኪሎ ስፖትም ስል ማዕከል የፋይ ግዥ ንብ አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 8 በመምጣት በ500 ብር አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመግዛት መውሰድ ይችላሉ።

8. ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 /አስር/ የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ የምትችሉ መሆኑንን እየገለፅን፣ ጨረታውን በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ላይ የሚያበቃና ሣጥኑም ታሽጎ በማግስቱ የሥራ ቀን ከሆነ ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ጨረታው የሚከፈት ሲሆን የሥራ ቀናት ካልሆነ ደግሞ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በማዕከሉ አዳራሽ ቁጥር 10 በግልፅ የሚከፈት ይሆናል።

9. ተጫራቾች ጨረታው በሚከፈትበት ዕለት ድርጅቱን የሚገልፅ ሕጋዊ መታወቂያና ውክልናን የሚገልፅ ደብዳቤ በመያዝ ጨረታው ሲከፈት መከታተል ይችላሉ፡።

1.0 ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ አየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ 10 /አስር / የሥራ ቀናት ውስጥ በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናልና ኮፒ (copy) አያይዘው በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ፋይ/ግዥ/ንብ አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 8 ሰነዱን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

11. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃ የጨረታ ሰነድ ከማስገባታቸው በፊት ናሙና የሚጠይቅበት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ካላቀረቡ ከጨረታው ውጪ ይሆናል። ጨረታው በግልፅ ከተከፈተ በኋላ ማንኛውንም መረጃ ዶከመንት ማቅረብ አይቻልም።

12. ለአሸናፊዎቹ ክፍያ የሚፈጸመው የተጠየቀውን ዕቃ በተጠየቀውና ባሸነፈው ናሙና መሠረት ሙሉ በሙሉ ወደ ንብረት ክፍል ገቢ ካደረገ በኋላ መሆኑን እናሳውቃለን።

13. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

14. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ በራሱ የትራንስፖርት አገልግሎት መ/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማስገባት ይጠበቅበታል።

15. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያገለግል የመጫረቻ ዋጋ ላይ ሲፒኦ /CPO ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

16. ተጫራቾች ከአሸነፉ በኋላ የውል ዋስትና 10% ሲፒኦ (CPO) ከባንክ የተረጋገጠ ማቅረብ የሚችል።

አድራሻ፡- አራት ኪሎ ስፖርት ትምህርትና ሥልጠና ማዕከል ቢሮ ቁጥር 8 ከሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አጠገብ የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ መሥሪያ ቤት ፊት ለፊት

ለበለጠ መረጃ ስልክ 0111261365

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስተዳደር የአራት ኪሎ ስፖርት፣ ትምህርትና ሥልጠና ማዕከል


Tender details

  • Deadline: 2026-10-07
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid closing (note): ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-08 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ላይ የሚያበቃና ሣጥኑም ታሽጎ በማግስቱ የሥራ ቀን ከሆነ ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Arat Kilo Sport Eduction and Training Center
  • Buyer address: አራት ኪሎ ስፖርት፣ ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ቢሮ ቁጥር 8 ከስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አጠገብ የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጅንሲ መስሪያ ቤት ፊት ለፊት
  • Bid bond: 10,000.00 (አስር ሺ ብር)
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 26, 2026)
  • Posted at: 2026-09-28T08:47:02.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders