Laboratory Equipment and Chemicals

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኦሮሚያ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን በ2019 ዓ/ም በጀት ዓመት ለላብራቶሪ ማዕከል አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልፅ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኦሮሚያ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን በ2019 ዓ/ም በጀት ዓመት ለላብራቶሪ ማዕከል አገልግሎት የሚውል፤ Lot-1(Laboratory Equipment and devices ), Lot-2(Laboratory work Bench) & Lot-3(Office Furniture) ከህጋዊ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች ያሉትን መሥፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ ተጋብዘዋል።

  • በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ ለተጨማሪ እሴት ታክሰ የተመዘገቡበት፤ መሆናቸውንና በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
  • ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር መኖራቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  • ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት እና የማይመለስ ብር 100/ መቶ/ ብር በመክፈል የኦሮሚያ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 11 የግዥና ፋይናንስ ክፍል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  • የጨረታ ማሰከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ(CPO)ብቻ በማቅረብ ተጫራቹ የዋጋውን 2% (ሁለት በመቶ) ማስያዝ ይኖርበታል።
  • ተጫራቾች የዕቃዎቹን የዋጋ ዝርዝር በጨረታ ማወዳደሪያ ለውድድር በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን፤ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን በማሰፈርና ማህተም በማድረግ ፤የጨረታ መወዳደሪያ ዶክመንቶችን፤

1- የቴክኒክ ዶክመንት ኦሪጅናልና ኮፒ ለየብቻ በተለያየ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቿል።

2- የፋይናንስ ዶክመንት ኦሪጂናልና ኮፒ ለየብቻ በተለያየ ፖስታ መቅረብ ይኖርባቿል።

  • በፖስታ ላይ የዶክመንቱን አይነት ማለትም ኦሪጅናል ወይም ኮፒ የሚል ፅሁፍ በመፃፍ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
  • ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 2/2/2019 ዓ/ም ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዛው ዕለት በ4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
  • የጨረታ ሣጥኑ ከታሸገ ወይም ከተከፈተ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  • የጨረታው አሸናፊ በራሱ ወጪ ዕቃዎቹን የመ/ቤቱ ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ አለበት።
  • መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 834 9814 / 09 11 35 00 00 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።

አድራሻ ሳርቤት አደባባይን ዞሮ ወደ ቄራ መሄጃ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መ/ቤቶች ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው።

የኦሮሚያ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን


Tender details

  • Deadline: 2026-10-12
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-10-12 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Oromia Environmental Protection Authority
  • Buyer address: ሣር ቤት አደባባይን  ዞሮ ወደ ቄራ መሄጃ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት መሥሪያ  ቤቶች  ቅጥር ገቢ ውስጥ
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 27, 2026)
  • Posted at: 2026-09-28T13:18:31.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders