Vehicles Purchase

ዲኬቲ ኢትዮጵያ (ድንቅ ክስተት ለጤና) ለድርጅቱ የቢሮ አገልግሎት የሚውል አንድ (01) አነስተኛ ኤስ.ዩ.ቪ (Small SUV) ተሽከርካሪ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ዲኬቲ ኢትዮጵያ (ድንቅ ክስተት ለጤና) የተባለ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን ማህበራዊ ግብይትን በመከተል የቤተሰብ እቅድን ለማስፋፋት፣ ኤችአይቪን ለመከላከል እንዲሁም የእናቶችና ህፃናት ጤናን ለመጠበቅ የሚያስችሉ ምርቶችን በማሰራጨት በሲቪል ማህበረሰብ ባለስልጣን በምዝገባ ቁጥር 0062 ተመዝግቦ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች በኤችአይቪ እና የስነ ተዋልዶ ጤና ላይ የራሱን አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ ያለ የውጭ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን፤ ለድርጅቱ የቢሮ አገልግሎት የሚውል አንድ (01) አነስተኛ ኤስ.ዩ.ቪ (Small SUV) ተሸከርካሪ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡

የተሸከርካሪው ዝርዝር መግለጫ (Vehicle Specification)

  • የተሽከርካሪው ዓይነት (Type): አነስተኛ ኤስ.ዩ.ቪ (Small SUV)
  • ሞዴል (Model): Toyota RAV4 Hybrid
  • የምርት ዘመን (Model Year): 2025 ወይም ከዚያ በላይ (2025 and above)
  • የሞተር መጠን (Engine Capacity): 2.5L ወይም ከዚያ በላይ፣ 4 ሲሊንደር (2.5L or more, 4 CYLINDER)
  • ማርሽ/ትራንስሚሽን (Transmission): CVT
  • የኤሌክትሪክ ሞተር ዓይነት (Electric Engine Type): Permanent Magnet Synchronous
  • የነዳጅ ዓይነት (Fuel System): ቤንዚን (Petrol)
  • የዊልቤዝ መጠን (Wheelbase): 2690 ሚ.ሜ (2690 mm)
  • የመቀመጫ ብዛት (Seating Capacity): 5 ሰው
  • ከመሬት ያለው ከፍታ (Ground Clearance): 200 ሚ.ሜ (200 mm)
  • የጎማ ዓይነት (Wheels): አልሙኒየም / 17 ኢንች (Aluminum / 17 inch)
  • የደህንነት ኤርባግ (Airbags): የጎን፣ የካርቴን፣ የሾፌር፣ የጎን ተሳፋሪ እና የሾፌር ጉልበት ኤርባግ (Side, Curtain, Driver, Passenger, Driver Knee)
  • ዋስትና (Warranty): 3 ዓመት ወይም 100,000 ኪ.ሜ (3 years / 100,000km)

የጨረታ ደንቦችና መመሪያዎች፡

1. ተጫራቾች በመስኩ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::

2. የመኪና ማስረከቢያ ቦታ፡ ከገርጂ ወደ ጉርድ-ሾላ በሚወስደው መንገድ ከጉና መጋዘን ቀጥሎ በሚገኘው መጋቢ መንገድ ላይ ወጋገን ባንክ ገባ ብሎ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት።

3. ተጫራቾች መኪናውን የሚያስረክቡበትን ትክክለኛ ጊዜ (Delivery Period) በሚያቀርቡት የዋጋ ማቅረቢያ (Quotation) ላይ በግልጽ ማመልከት አለባቸው፡፡

4. የጨረታ ማስገቢያ የመጨረሻ ቀን፡ መስከረም 27/2019 ከሰዓት 11:00

5. የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት፡ መስከረም 28/2019 ከሰዓት 8:00

6. የጨረታ መክፈቻ ቦታ፡ በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት የስብሰባ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተባለው ቀንና ሰዓት ባይገኙም ጨረታው የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን፡፡

7. ድርጅቱ ማንኛውንም ጨረታ በሙሉ ወይም በከፊል ያለምንም ግዴታ የመቀበል ወይም የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር፡ +251 911 317 100 / +251 911 357 228


Tender details

  • Deadline: 2026-10-07
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid opening: 2026-10-08 14:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: DKT ETHIOPIA
  • Buyer address: Kirkos sub-city, woreda 02, House No.177
  • Published on: Reporter (Sep 27, 2026)
  • Posted at: 2026-09-28T14:33:22.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders