Chemicals and Reagents

የግዮን ሆቴሎች ድርጅት የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ የግዮን ሆቴሎች ድርጅት

  • ሎት 1 የዋና ገንዳ ትሪትመንት ኬሚካሎች ግዥ
  • ሎት 2 የፅህፈት መሳሪያ ዕቃዎች ግዥ
  • ሎት 3 የኮንፎርት ከቨር፤ ተዛማጅ ዕቃዎች እና የመጋረጃ ግዥ
  • ሎት 4 የምግብ ማደራጃ መሳሪያዎች /ማሽነሪዎች/ ግዥ
  • ሎት 5 የፕሪንተር የፎ ቶኮፒ ማሽን ጥገና እና የቀለም ሙሌት የአግልግሎት ግዥ

ከላይ በሎት ለተገለፁት ዝርዝር መሠረት ዕቃዎች እና የአገልግሎት ግዥ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

  • የ2018 በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያለው
  • TIN No /የግብር መለያ ቁጥር/ ሰርተፍኬት ያለው
  • VAT/ ተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት ያለው
  • የገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል
  • የተጠቀሱትን የአገልግሎት እና የዕቃ ግዥ ልምድ ቢኖራቸው ይመረጣል፤
  • ለሎት 5 በፎቶኮፒ ማሽን እና በፕሪተር ጥገና በቂ የሆነ የስራልምድ ያለውና ማቅረብ የሚችል፤
  • በሎት 3 እና ሎት 4 እንዲሁም በሎት 5 ተወዳድረው አሸናፊ የሚሆኑ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ እና የቅድሚያ ክፍያ % በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ በማስያዝ ውል መዋዋል የሚችሉ መሆን አለባቸው
  • የመጋረጃ ግዥ ተጫራቾች ድርጅቱ በሚያቀርባለቸው ሳምፕል መሰረት የሚሰሩና መጋረጃ የሚሰራላቸው ክፍሎችን ቀድመው በመለካት የዕቃና የዕጅ ዋጋ በማስላት የሚሰጡ መሆን አለባቸው
  • በሚወዳደሩባቸው የጨረታ ዘርፎች ለሚያቀርቡት ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ማስያዝ የሚችሉ፤ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ ከአዲስ አበባ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል።
  • ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ለእያንዳንዱ ጨረታ ብር 500.00 /አምስት መቶ/ በዋናው እንግዳ መቀበያ በመክፈል ለእያንዳንዱ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከፋሲሊቲ መምሪያ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።
  • የጨረታው ሳጥን የጨረታ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ በወጣበት በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ጨረታው የሚከፈትበት የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
  • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 551 3222 Ext 5429/5163 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
  • የሥራ ሰዓት፡ ከሰኞ እስከ ሀሙስ ጠዋት 2፡00 – 6፡00 ከሰዓት 7፡00 – 11፡00
    - አርብ ጠዋት ከ2፡00 5፡30 ከሰዓት 7፡30 እስከ 11፡00
  • ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ለመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

Tender details

  • Deadline: 2026-10-12
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ በወጣበት በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-12 12:00
  • Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ በወጣበት በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ghion Hotels Enterprise
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: ለእያንዳንዱ ጨረታ ብር 500.00 /አምስት መቶ/
  • Published on: Reporter (Sep 27, 2026)
  • Posted at: 2026-09-28T14:48:35.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders