Catering and Cafeteria Services
የአዳማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለብቃት ፕሮጀክት የምሣ፣ ሪፍረሽመንት እና ውሃ አገልግሎትን በአዳማ ከተማ ውስጥ የሚገኙትን ተወዳዳሪዎቸን /ካፌና ሬስቶራንቶችን/ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዳማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለብቃት ፕሮጀክት የምሣ፣ ሪፍረሽመንት እና ውሃ አገልግሎትን በአዳማ ከተማ ውስጥ የሚገኙትን ተወዳዳሪዎቸን /ካፌና ሬስቶራንቶችን/ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
ለተጠየቀው የሥራ አቅርቦት ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tax payer registration No) ያላቸው
1. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ ብር) በሲንቄ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 10545511611211 ላይ ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ከመስከረም 20 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ ቀናት በጽ/ቤቱ የግዢ የሥራ ሂደት ቢሮ ድረስ በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
2. ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመክፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. ማንኛውም ተጫራች በሚወዳደርበት ሰነድ ላይ በተሰጠው ስፔሲፊኬሽን መሰረት ብቻ ሳይጨምር ወይም ሳይቀንስ ዋጋውን መሙላት ይኖርበታል።
4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የተጠቀሰውን ማስረጃዎች ኦሪጅናልና ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
5. ጨረታው የሚከፈተው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን የስራ ቀን ከሆነ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በአዳማ ከተማ ገንዘብ/ፅ/ቤት ሶስተኛ ፎቅ ግዢ ክፍል ውስጥ ይከፈታል። እለቱ በዓል ወይም መ/ቤቱ ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።
6. የጨረታው አሸናፊ በጨረታ መመሪያ በተሰጠው መሠረት የጨረታ አሸናፊነቱ በውስጥ ማስታወቂያና በስልክ እንደተገለፀ አስፈላጊውን የጨረታ ውል ከአዳማ ከተማ ገንዘብ ፅ/ቤት ጋር መፈራረም አለበት። ይህ ባይፈፀም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ገቢ ይሆናል።
7. ማንኛውም ተጫራች ለውድድር የሚቀርበው ቫት ተጠቃሚ ሲሆን ፣ 7.5% በክፍያ ግዜ የሚቀነስ ይሆናል።
8. መሥሪያ ቤቱ ከሚያደርገው የግዢ ውል 20 ፐርሰንት መጨመር ወይም መቀነስ የሚችል መሆኑን ተጫራቹ መገንዘብ አለበት።
9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 /መቶ ሺህ/ ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
10. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በአዳማ ከተማ መስተዳድር የአዳማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-15
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን የስራ ቀን ከሆነ በ4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-15 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን የስራ ቀን ከሆነ በ4፡30 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Adama City Finance and Economic Development Bureau
- Bid bond: 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ
- Published on: Addis Zemen (Sep 30, 2026)
- Posted at: 2026-09-30T11:43:51.000Z
- Source: Qelal Tenders