Products and Services

የቡራዩ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለስልጠና የሚያስፈልጉትን የተለያዩ እቃዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የቡራዩ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለስልጠና የሚያስፈልጉትን የግብርና ስራ ፤ የኮንስትራክሽን ፤ የICT ፤ የኤሌክትሪክ፣ የቧንቧ፣ አውቶሞቲቭ ፣ የደንብ ልብስ ፤ የፈርኒቸር ፤ የኢንዱስትሪያል ኤሌክትሪክ ሲቲ፤ GMFA፤ ለ Hair dressing ስልጠና የሚውሉ እቃዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ዝርዝር ሁኔታዎች

ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከቡራዩ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የማይመለስ ብር. 2000.00(ሁለት ሺህ ብር) በመክፈል ስለዕቃዎቹ የሚገልፅ ሰነድ (ዶክመንት) ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከቡራዩ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 11 ዘውትሪ በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።

1. በዕቃ ዓይነት የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ በስማቸው ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2. ግዥዉ(አገልግሎቱ) ከ100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ) ብር በላይ ከሆነ የቫት (የተጨማሪ እሴት ታክስ) ተመዝጋቢና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለዉ፡፡ እንዲሁም በፌዴራል ገ/ኢ/ልማት ሚኒስቴር ወይም በኦሮሚያ ገ/ኢ/ል/ቢሮ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3.ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተመሰከረ ወይም CPO (ሲፒኦ) የጨረታ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸዉ።

4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሙላት በሰም በታሽገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እሰከ 16ኛ ቀን ከቀኑ 4:00 ቢሮ ቁጥር 06 ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት ይችላሉ።

5 ጨረታው 16ኛው ቀን የስራ ቀን ከልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን 4፡30 ላይ ይሆናል በዚሁ በዕለቱ ተጨራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

6 ኮሌጁ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች (0913 154 549) መደወል ይችላሉ

የቡራዩ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-19
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እሰከ 16ኛ ቀን ከቀኑ 4:00
  • Bid opening: 2026-10-19 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እሰከ 16ኛ ቀን ከቀኑ 4:30
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Burayu Polytechnic College
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 2,000.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 04, 2026)
  • Posted at: 2026-10-05T11:54:12.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders