Health Related Services and Materials
ሰዎች ለሰዎች ድርጅት በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች ለሚያከናውናቸው የጤና ስራዎች የሚውሉ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች ከሀገር ውስጥ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Health Related Services and MaterialsHealth Care, Medical IndustryMedical Equipment and Supplies
Addis Ababa
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ሰዎች ለሰዎች ድርጅት በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች ለሚያከናውናቸው የጤና ስራዎች የሚውሉ
- የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች ከሀገር ውስጥ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት ማቅረብ ከሚችሉ እና ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ከሚችሉ ህጋዊ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ እንድትወዳደሩ ተጋብዛችኋል። ተወዳዳሪዎች ማሟላት የሚገባቸው
- በዘርፉ የተሰማሩበት የ2019 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው፤
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN Number) ማቅረብ የሚችሉ እና
- የዘመኑን ግብር የከፈሉትን እና የታክስ ክሊራንስ ባለስልጣን በጨረታ ለመሳተፍ የተጻፈ የታደሰ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ህጋዊ ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ አዲስ አበባ በሚገኘው የሰዎች ለሰዎች ድርጅት ማስተባበሪያ ቢሮ በመቅረብ በማይመለስ ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር) በመግዛት እንዲሳተፉ ይጋበዛል። የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ከላይ የተጠቀሱትን 4 ሰነዶች ማሳየት ግዴታ ነው። የጨረታ ሰነዱን ያልገዛ ተጫራች በጨረታው መሳተፍ አይችልም።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ይሆን ዘንድ ባቀረቡት ዋጋ ልክ (የተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ) 2% በሲፒኦ (CPO) ብቻ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት አዲስ አበባ በሚገኘው የሰዎች ለሰዎች ድርጅት ማስተባበሪያ ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-6 ያሉትን ካላሟሉ ከጨረታ ይሰረዛሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ የሰዎች ለሰዎች ድርጅት ያዘጋጀውን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ መጠቀም አለባቸው። ተጫራቾች የሚያቀርቡት የእያንዳንዱ እቃ ዋጋ ሰዎች ለሰዎች ድርጅት ላቀረበው የዕቃው አይነት እና መግለጫ መስፈርት (Specification) መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ እና የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በአንድ ፖስታ ሌሎች የተጠየቁ የንግድ ሰነዶችን (Business Document) እና የእቃውን አይነት መግለጫ መስፈርት (Specification) በሌላ ፖስታ አሽጎ ማስገባት አለባቸው። ፖስታዎቹም የዋጋ ማቅረቢያ እና የእቃውን አይነት መግለጫ መስፈርት (Technical) ሰነድ ተብለው ተጽፎባቸው ይቀርባሉ
- ዋጋ በሚሞሉበት ጊዜ የተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ የእያንዳንዱ እቃ ዋጋ በትክክል መሞላት አለበት። አቅርቦቱ የተጨማሪ እሴት ታክስ የማይመለክተው ከሆነ በሚሰጡት ዋጋ ላይ የተጨማሪእሴት ታክስ አይካተትም።
- ተጫራቾች የአንዱን ዋጋ ከሞሉ በኋላ ጠቅላላ ድምሩን ወደ ጎን እና ወደ ታችም ደምረው ማስቀመጥ አለባቸው፡፡ የድምር ስህተት ቢኖር የተሰጠው ነጠላ ዋጋ ተቀባይነት ይኖረዋል።
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን መፈረም እና ድርጅታቸውን ማህተም ማድረግ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በተቀመጠው የዕቃ ዝርዝር በተናጠል ለእያንዳንዱ እቃ አነስተኛ ዋጋ ያቀረበ ተወዳዳሪ ይሆናል።
- በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፤ ስርዝ ድልዝ ካለ በአቅራቢው መፈረም አለበት።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር የሥራ ቀናት ይቆያል። በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰዎች ለሰዎች ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤት ቦሌ ቡልቡላ ወረዳ 12 ቀይ አፈር አካባቢ በሚገኘው አዳራሽ ይከፈታል። አስረኛው ቀን ቅዳሜ እሁድ ኣልያም በበዓል ቀን ላይ ከዋለ በቀጣይ የስራ ቀን ይሆናል።
- አሸናፊ የሚሆነው ተጫራች ጥራቱን በጠበቀ መንገድ ዕቃውን አሟልቶ በሶስት የስራ ቀናቶች ማቅረብ ይኖርበታል፤ ነገር ግን ጥራቱ በድርጅቱ ተረጋግጦ ካልተቀበለው ቀይ የማምጣት ግዴታ አለበት፤ ይህን ባያደርግ ግን እቃውን ማቅረብ እንዳልቻለ ይቆጠራል፤ ያስያዘ የሲፒኦ ገንዘብ (ላሸነፈው ዕቃ) ለድርጅቱ ገቢ ይደረጋል።
- አሸናፊ የሆነው አቅራቢ ክፍያ በሚጠይቅበት ጊዜ ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ አለበት። ይህንን ማቅረብ የማይችል ከሆነ ምንም አይነት ክፍያ መጠየቅ አይችልም። መ/ቤቱም እንዲከፍል አይገደድም።
- በዚህ ማስታወቂያ ያልተገለጹ ሌሎች ህጎች በሀገሪቱ ወይም በድርጅቱ የግዥ አፈፃፀም መመሪያ መሰረት ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል።
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ለ Menschen fur Menschen ስም አዘጋጅተው በፓስታ በማሸግ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው ውጤት ጨረታ ተገምግሞ እንዳለቀ በደብዳቤ ወይም በውስጥ ማስታወቂያ የሚገለጽ ይሆናል።
- ተጫራቾች ሌላ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ መስጠት አይችሉም።
- በጨረታው ተሳትፎ አሸናፊ የሆነ ተወዳዳሪ ያሸነፈውን እቃ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ማቅረብ ካልቻለ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ (ላሸነፈው ዕቃ) ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል።
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011 471 4291 / 011 471 4353 በስራ ሰዓት ደውለው ማግኘት ይችላሉ።
ሰዎች ለሰዎች ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-10-19
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-19 14:30
- Bid opening (note): በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8:30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Menschen für Menschen Foundation (MfM)
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 1,000 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 08, 2026)
- Posted at: 2026-10-08T13:21:54.000Z
- Source: Qelal Tenders