Vehicles Purchase

የኢትዮጵያ የእንስሳት ሐኪሞች ማኅበር (Ethiopian Veterinary Association-EVA) ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሠራ አዲስ ተሽከርካሪ (Brand New Fully Electric Vehicle) ከሀገር ውስጥ ገበያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በአስቸኳይ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የኤሌክትሪክ መኪና ለመግዛት በድጋሜ የወጣ አስቸኳይ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር፡ EVA/NCB/EV/04/2026

የኢትዮጵያ የእንስሳት ሐኪሞች ማኅበር (Ethiopian Veterinary Association-EVA) ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሠራ አዲስ ተሽከርካሪ (Brand New Fully Electric Vehicle) ከሀገር ውስጥ ገበያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በአስቸኳይ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም በዘርፉ የተሠማሩ፣ ብቃት ያላቸውና ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መሥፈርቶችን የሚያሟሉ አቅራቢ ድርጅቶች በጨረታው ላይ እንዲሳተፉ ማኅበሩ ይጋብዛል::

1. መቅረብ የሚገባቸው ሕጋዊ ማስረጃዎች (Eligibility Criteria) ፤

1.1. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ሴርቴፊኬት፣

1.2. በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) መመዝገባቸው የሚያሳይ ሴርቴፊኬት፣

1.3. የ2018 ዓ.ም ግብር የተከፈለበት ማስረጃ፣

1.4. ለ2019 የግብር ዘመን የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ አሊያም በጨረታ ለመወዳደር እንደሚችሉ ከገቢዎች ሚኒስቴር የተሰጠ የግብር ክሊራንስ (Tax Clearance) መረጃ፣

1.5. በግዥና ንብረት ባለሥልጣን የአቅራቢዎች ዝርዝር (Federal Procurement Public Agency Web) ውስጥ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ወይም ሴርቴፊኬት፣

2. የጨረታ ሰነድ አወሳሰድ፤

2.1. ፍላጎት ያላቸውና መስፈርቱን የሚያሟሉ ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 16 (አሥራ ስድስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ በማኅበሩ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 303/306 ዘወትር በሥራ ሰዓት በአካል ቀርበው የጨረታ ሰነዱን በነጻ መውሰድ ይችላሉ።

2.2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በጥሬ ገንዘብ፣ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም CPO ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። ጨረታውን ያላሸነፉ ተወዳዳሪዎች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ዋስትና፤ አሸናፊ ድርጅት እንደተለየ ወዲያኑ ይመለስላቸዋል።

2.3. ተጫራቾች የቴክኒክ ሰነድ ኦሪጂናል እና የፋይናንሻል ሰነድ ኮፒ ለየብቻው በታሽገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ መ/ቤታችን ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።

2.4. ጨረታው በ16ኛው ቀን በ11፡30 ላይ ይዘጋል። በ17ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ሆኖም የተጫራቾች ወይም የወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታውን መክፈት ሂደት አያስተጓጉልም።

2.5. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ፦

  • በስልክ ቁጥር:- +251-11 552 5020; 09 11 89 49 02 09; 09 04 32 76 08; 09 11 18 55 03
  • አድራሻ፦ ከእንግሊዝ ኢምባሲ (British Embassy) ወደ School of Tomorrow በሚወስደው መንገድ 300 ሜትር ገባ ብሎ ይመናሹ ሕንጻ ፊት ለፊት ያገኙናል።

የኢትዮጵያ የእንስሳት ሐኪሞች ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-10-22
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-23 10:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በ17ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Veterinary Association
  • Buyer address: ከእንግሊዝ ኢምባሲ (British Embassy) ፊት ለፊት 600 ሜትር ገባ ብሎ ወደ School of Tomorrow በሚወስደው መንገድ፣ ይመናሹ ሕንጻ አጠገብ እንገኛለን።
  • Bid bond: 2%
  • Published on: Reporter (Oct 07, 2026)
  • Posted at: 2026-10-08T14:55:35.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders