Vehicles Purchase

የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት Middle Floor Manual Transmission Bus (የማሰልጠኛ አውቶቡስ) አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አአከአአድ/ ብግጨቁ/016/2019

የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ በግዥ መለያ ቁጥር አአከአድ/ብግጨቁ/016/2019 Middle Floor Manual Transmission Bus (የማሰልጠኛ አውቶቡስ) አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም በመስኩ የተሰማሩና ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው አቅራቢዎች (ድርጅቶች) ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን፡-

1. በዘርፉ የተሰማራ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ኮፒ (Valid Trade Licensee)፣

2. በመንግስት ግዥ ላይ ለመሳተፍ የአቅራቢዎች ዝርዘር ውስጥ ስለመግባቱ በድረ-ገፅ የተመዘገበበት ኮፒ፣

3. የታክስ ከፋይ የምዝገባ ሰርተፍኬት፣

4. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት ኮፒ (VAT Certificate)፣

5. በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ፈቃድ (Valid Tax Clearance Certificate)፣

6. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ ብር 1,500,000.00 (አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ) በማቅረብ በግልጽ ጨረታው ላይ መወዳደር ይችላሉ።

በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ አቅራቢዎች (ድርጅቶች) ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ እስከ ምሳ ሰዓት (6፡00 ሰዓት) የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በጥሬ ገንዘብ በመክፈል በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ 22 እየሩስ ህንጻ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋናው መ/ቤት (ማዕከል) የግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 ወይም 7-01 መውሰድ ይችላሉ።

ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናል እና ኮፒ በመለየት እስከ ጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ በግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

ጨረታው ጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ጠዋት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 ይከፈታል።

ማሳሰቢያ፤

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር: 0116663206
አዲስ አበባ የከተማ
አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-29
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-10-29 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa City Bus Service Enterprise
  • Bid bond: 1,500,000.00 (አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Oct 09, 2026)
  • Posted at: 2026-10-09T09:33:14.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders