Chemicals and Reagents

የወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በ2019 በጀት ዓመት ለስራ ክፍሎች የሚያገለግሉ መድኃኒቶችን፣ የላብራቶሪ ሪኤጀንቶችን ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በ2019 በጀት ዓመት ለስራ ክፍሎች የሚያገለግሉ፡-

  • ሎት 1- መድኃኒቶችን
  • ሎት 2- የላብራቶሪ ሪኤጀንቶችን ለመግዛት ይፈልጋል።

ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ስለዕቃዎች የሚገልፅ ሰነድ (ዶክመንት) በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይድ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 302 በመቅረብ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላል።

1. ተጫራቾች ተፈላጊ ዕቃዎችን ማቅረብ የሚያስችላቸውን የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) እና የታደሰ የምግብና የመድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን የምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

2. የዚህ ጨረታ ተካፋዮች በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፣ የምስክር ወረቀት ያላቸውና ኮፒውን ማቅረብ አለባቸው።

3. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ዋጋ 20,000 በባንክ በተመሰከረ CPO /ሲፒኦ/ የጨረታ ዋስትና ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።

4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ላይ በተለያዩ ፖስታዎች ሰነድ አንድ ኦርጂናል እና አንድ ኮፒ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት 2፡30 6፡30 ሰዓት፣ ከሰዓት ከ7፡30-11፡30 ሰዓት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ክፍል ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

5. ጨረታው በ15ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከሰዓት በኋላ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል። የመክፈቻውም ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በህዝባዊ በዓላት ላይ ከዋለ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

6.ሆስፒታሉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 046 329 9263 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

የወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል


Tender details

  • Deadline: 2026-10-24
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-24 14:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን በ8፡30 ሰዓት
  • Region: Central Ethiopia
  • Publishing entity: Worabe Comprehensive Specialized Hospital
  • Bid bond: 20,000.00 ብር
  • Bid document price: 400.00 /አራት መቶ ብር/
  • Published on: Addis Zemen (Oct 09, 2026)
  • Posted at: 2026-10-10T08:10:32.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders