Architectural and Construction Design
የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን በተለያዩ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች የመንገድ ዲዛይን አማካሪዎችን ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል
Description
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዢ መለያ ቁጥር፡- ሲ/መ/ባ/001/2018
የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን በተለያዩ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች የመንገድ ዲዛይን አማካሪዎችን ከዚህ በታች በተገለጸው መሠረት መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
|
Lot-2 |
|||||
|
I |
Project Name |
Length in k.m |
Project Location |
Distance From Zonal town (KM) |
|
|
Woreda |
Zone |
||||
|
1 |
Alawo arke-sadamo dikicha |
7 |
Borcha |
Northern zone |
|
|
2 |
Tula dikko hula asphalit |
7 |
Hagere selam |
Southern zone |
|
|
3 |
Hariro-badalcha bilate |
11 |
Bilate zura |
Northern zone |
|
|
4 |
Foqa-badalicha bilate masalitegna |
20 |
Darara |
Centeral zone |
|
|
5 |
Dananche gufache-2 |
12 |
Wondo genet |
Northern zone |
|
|
6 |
Abara-bute |
13.5 |
Darara |
Southern zone |
|
|
7 |
Odiboko arawe |
7 |
Hook |
Eastern zone |
|
|
8 |
Odiboko marimara |
9.5 |
Holo |
Eastern zone |
|
|
9 |
Echama-shiko finchawa |
9 |
Daela |
Eastern zone |
|
|
10 |
Shaman garmama bilate |
15 |
Bilate |
Northern zone |
|
|
|
Total |
111 |
|
|
|
1. ተጫራቾች ማቅረብ ያለባቸው ማስረጃዎች
ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ከከተማ ልማትና ግንባታ ሚኒስቴር፣ የፌዴራል ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኢትዮጵያ፣ ወይም ከክልል ግንባታና ከተማ ልማት ቢሮ የተሰጠ እና ለአሁኑ የበጀት ዓመት የሚያገለግል የአማካሪ አገልግሎት፣ የሀይዌይና ድልድይ ደረጃ-3 እና ከዚያ በላይ የሆነ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ እንዲሁም ተጫራቹ የጨረታውን መስፈርት ማሟላቱን የሚያረጋግጡ ሌሎች ተገቢ ሰነዶችን ማቅረብ አለባቸው። እነዚህም፦
- ለአሁኑ በጀት ዓመት የሚያገለግል የንግድ ፈቃድ፤
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤
- ለአሁኑ የበጀት ዓመት የሚያገለግል ከከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተሰጠ የአማካሪ ብቃት ምስክር ወረቀት፤
- የቫት (VAT) ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤
- የግብር ከፋይ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤
- በጨረታ ለመሳተፍ በሕጋዊ አካል የተሰጠ እና ቢያንስ የጨረታ ማቅረቢያ ቀን ላይ የሚያገለግል የፈቃድ ምስክር ወረቀት፤
- በፌዴራል የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ (FPPPAA) የተመዘገበ አቅራቢ መሆንን የሚያረጋግጥ ማስረጃ።
2. የጨረታ ሰነዶች አቀራረብ፤ተጫራቾች ሶስት የተለያዩ ፖስታዎችን ማቅረብ አለባቸው፦
- የብቃት መረጃ (Qualification Information) – አንድ ኦሪጅናል በተለየ ፖስታ ታሽጎ እና ሁለት ቅጂዎች እያንዳንዳቸው በተለየ ፖስታ ታሽገው፣ በመጨረሻም በአንድ ውጫዊ ፖስታ ውስጥ መታሸግ አለባቸው።
- የጨረታ ዋስትና (Bid Security)፤
- የገንዘብ ጨረታ (Financial Bid - አንድ ኦሪጅናል በተለየ ፖስታ ታሽጎ እና ሁለት ቅጂዎች እያንዳንዳቸው በተለየ ፖስታ ታሽገው፣ በመጨረሻም በአንድ ውጫዊ ፖስታ ውስጥ መታሸግ አለባቸው።
- በመጨረሻም እነዚህ ሶስት የውስጥ ፖስታዎች በአንድ ውጫዊ ፖስታ ውስጥ ታሽገው መቅረብ አለባቸው።
3. የጨረታ ግምገማ፤የጨረታ ግምገማው በሁለት ደረጃዎች ይከናወናል፡ በመጀመሪያ የብቃት መረጃ ይገመግማል በሁለተኛ ደረጃ ብቁ ለሆኑ ተጫራቾች የገንዘብ ጨረታ ይከፈትና ይገመግማል።
4. የጨረታ ሰነድ መመልከትና ተጨማሪ መረጃ
ፍላጎት ያላቸው ብቁ ተጫራቾች ከታች በተጠቀሰው አድራሻ የጨረታ ሰነዱን መመልከትና ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።ከሰኞ እስከ ሐሙስ፦ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 12፡30 እና ከሰዓት 7፡30 እስከ 11፡30፤ዓርብ፦ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 5፡30 እና ከሰዓት 7፡30 እስከ 11፡30።
5. የጨረታ ሰነድ ግዢ
በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን ሙሉ የጨረታ ሰነድ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች በጽሑፍ ማመልከቻ በማቅረብ እና ለእያንዳንዱ ሰነድ 1,000 (አንድ ሺህ) ብር የማይመለስ ከፍያ በመፈጸም በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
የጨረታ ሰነዱ የሚሸጠው ይህ ማስታወቂያ በኢትዮጵያ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ የቀን መቁጠሪያ ቀናት ይሆናል።
የመጨረሻ የጨረታ ማቅረቢያ እና የጨረታ መክፈቻ በዚህ ማስታወቂያ በኢትዮጵያ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ከ22ኛው ቀን በ4፡00 ጥዋት እና 4፡30 ጥዋት በቅደም ተከተል ይከናወናል። 22ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ፣ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከናወናል።
6. የጨረታ ማቅረቢያና የጨረታ ዋስትና
ጨረታዎች ከላይ በተጠቀሰው ቀን ከ4፡00 ጥዋት በፊት ወይም በዚያው ሰዓት ከታች በተጠቀሰው አድራሻ መድረስ አለባቸው።
ጨረታው ከ200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር የጨረታ ዋስትና ጋር መቅረብ አለበት። የጨረታው ተፈጻሚነት ጊዜ 120 (አንድ መቶ ሃያ) ቀናት ይሆናል። ከተወሰነው ጊዜ በኋላ የሚቀርቡ ጨረታዎች አይቀበሉም።
7. ቀደም ሲል ከሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን ጋር የሠሩ አማካሪዎች ከዚህ በፊት ከሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን ጋር ሠርተው፦
የተሰጣቸውን ሥራ ቢያንስ 70% ያላጠናቀቁ፤ከባለሥልጣኑ የድጋፍ የምከር ደብዳቤ የሌላቸው፣ በቀደሙት የመንገድ ድልድይ ዲዛይን ሥራዎች የመጨረሻ ተቀባይነት (Final Acceptance) ያላስፈጸሙ፤ እና የመጨረሻ ረቂቅ ሪፖርቶችን በSoft Copy እና Hard Copy ሙሉ በሙሉ እስከዚህ ጨረታ መዝጊያ ቀን ድረስ ያላስረከቡ፣በዚህ ጨረታ መሳተፍ አይችሉም።
8. በአንድ በላይ ሎት መሳተፍ፤አንድ ተጫራች በዚህ የመንገድ ዲዛይን አማካሪ አገልግሎት ከአንድ በላይ ሎት ላይ መሳተፍ አይችልም።
9. የባለሥልጣኑ መብት፤የሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን የጨረታውን ሂደት በከፊል ወይም በሙሉ የመቀበል ወይም የመሰረዝ መብቱን የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር፡- 0462-128-446/ ሀዋሳ
ሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን
Tender details
- Deadline: 2026-10-31
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በኢትዮጵያ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ከ22ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-31 10:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በኢትዮጵያ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ከ22ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት
- Region: Sidama
- Publishing entity: Sidama Region Road Authority
- Bid bond: 200,000.00 ብር
- Bid document price: 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/ ለእያንዳንዱ
- Published on: Addis Zemen (Oct 10, 2026)
- Posted at: 2026-10-10T08:30:15.000Z
- Source: Qelal Tenders