Engineering
የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን በተለያዩ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች የመንገድ ዲዛይን አማካሪዎችን ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል
Description
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዢ መለያ ቁጥር፡- ሲ/መ/ባ/001/2018
የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን በተለያዩ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች የመንገድ ዲዛይን አማካሪዎችን ከዚህ በታች በተገለጸው መሠረት መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
|
Lot-1 |
|||||
|
I |
Project Name |
Length in k.m |
Project Location |
Distance From Zonal town (KM) |
|
|
Woreda |
Zone |
||||
|
1 |
Taratu bokola |
10.4 |
Chire |
Eastern zone |
|
|
2 |
Welle magado |
3 |
Hook |
Eastern zone |
|
|
3 |
Majo odiganbo |
20 |
Haroresa |
Eastern zone |
|
|
4 |
Chire karate gubo hema |
40 |
Chire |
Eastern zone |
|
|
5 |
Boa lelo |
11 |
Wonsho |
Centeral zone |
|
|
6 |
Girja wele |
15 |
Hoko |
Eastern zone |
|
|
7 |
Gidawo asphalt adote qacha |
1.8 |
a/wondo |
Southern zone |
|
|
8 |
Yuwo bine bolancho |
5.2 |
w/genet |
North zone |
|
|
9 |
Dawale balo |
2.5 |
Wonsho |
Southern zone |
|
|
10 |
Machisho corderete kacha |
1.5 |
Dara |
Northern zone |
|
|
11 |
Huro tiwiro gonjowe |
12 |
Bansa |
Eastern zone |
|
|
|
Total |
123.4 |
|
|
|
1. ተጫራቾች ማቅረብ ያለባቸው ማስረጃዎች
ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ከከተማ ልማትና ግንባታ ሚኒስቴር፣ የፌዴራል ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኢትዮጵያ፣ ወይም ከክልል ግንባታና ከተማ ልማት ቢሮ የተሰጠ እና ለአሁኑ የበጀት ዓመት የሚያገለግል የአማካሪ አገልግሎት፣ የሀይዌይና ድልድይ ደረጃ 3 እና ከዚያ በላይ የሆነ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ እንዲሁም ተጫራቹ የጨረታውን መስፈርት ማሟላቱን የሚያረጋግጡ ሌሎች ተገቢ ሰነዶችን ማቅረብ አለባቸው። እነዚህም፦
- ለአሁኑ በጀት ዓመት የሚያገለግል የንግድ ፈቃድ፤
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤
- ለአሁኑ የበጀት ዓመት የሚያገለግል ከከተማ ልማትና ግንባታ ሚኒስቴር የተሰጠ የግንባታ ብቃት ምስክር ወረቀት፤
- የቫት (VAT) ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤
- የግብር ከፋይ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤
- በጨረታ ለመሳተፍ በሕጋዊ አካል የተሰጠ እና ቢያንስ የጨረታ ማቅረቢያ ቀን ላይ የሚያገለግል የፈቃድ ምስክር ወረቀት፤
- በፌዴራል የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ (FPPPAA) የተመዘገበ አቅራቢ መሆንን የሚያረጋግጥ ማስረጃ።
2. የጨረታ ሰነዶች አቀራረብ ተጫራቾች ሶስት የተለያዩ ፖስታዎችን ማቅረብ አለባቸው፡
- የብቃት መረጃ (Qualification Information) - አንድ ኦሪጅናል በተለየ ፖስታ ታሽጎ እና ሁለት ቅጂዎች እያንዳንዳቸው በተለየ ፖስታ ታሽገው፣ በመጨረሻም በአንድ ውጫዊ ፖስታ ውስጥ መታሸግ አለባቸው።
- የጨረታ ዋስትና (Bid Security)
- የገንዘብ ጨረታ (Financial Bid - አንድአሪጅናል በተለየፖስታ ታሽጎ እና ሁለት ቅጂዎች እያንዳንዳቸው በተለየ ፖስታ ታሽገው፣ በመጨረሻም በአንድ ውጫዊ ፖስታ ውስጥ ታሽግ አለባቸው።
- በመጨረሻም እነዚህ ሶስት የውስጥ ፖስታዎች በአንድ ውጫዊ ፖስታ ውስጥ ታሽገው መቅረብ አለባቸው።
3. የጨረታ ግምገማ፤የጨረታ ግምገማው በሁለት ደረጃዎች ይከናወናል፦በመጀመሪያ የብቃት መረጃ ይገመግማል፣በሁለተኛ ደረጃ ብቁ ለሆኑ ተራቾች የገንዘብ ጨረታ ይከፈትና ይገመግማል።
4. የጨረታ ሰነድ መመልከትና ተጨማሪ መረጃ
ፍላጎት ያላቸው ብቁ ተጫራቾች ከታች በተጠቀሰው አድራሻ የጨረታ ሰነዱን መመልከትና ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።ከሰኞ እስከ ሐሙስ፦ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30 እና ከሰዓት 7፡30 እስከ 11፡30፤ ዓርብ፦ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 5፡30 እና ከሰዓት 7፡30 እስከ 11፡30።
5. የጨረታ ሰነድ ግዢ
በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን ሙሉ የጨረታ ሰነድ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች በጽሑፍ ማመልከቻ በማቅረብ እና ለእያንዳንዱ ሰነድ 1000 (አንድ ሺህ) ብር የማይመለስ ከፍያ በመፈጸም በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ። የጨረታ ሰነዱ የሚሸጠው ይህ ማስታወቂያ በኢትዮጵያ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ለ 21 ተከታታይ የቀን መቁጠሪያ ቀናት ይሆናል።
የመጨረሻ የጨረታ ማቅረቢያ እና የጨረታ መክፈቻ በዚህ ማስታወቂያ በኢትዮጵያ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ከ22ኛው ቀን በ4፡00 ጥዋት እና 4፡30 ጥዋት በቅደም ተከተል ይከናወናል። 22ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ፣ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከናወናል።
6. የጨረታ ማቅረቢያና የጨረታ ዋስትና
ጨረታዎች ከላይ በተጠቀሰው ቀን ከ4፡00 ጥዋት በፊት ወይም በዚያው ሰዓት ከታች በተጠቀሰው አድራሻ መድረስ አለባቸው።
ጨረታው ከ200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር የጨረታ ዋስትና ጋር መቅረብ አለበት፡፡ የጨረታው ተፈጻሚነት ጊዜ 120 (አንድ መቶ ሃያ) ቀናት ይሆናል። ከተወሰነው ጊዜ በኋላ የሚቀርቡ ጨረታዎች አይቀበሉም።
7. ቀደም ሲል ከሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን ጋር የሠሩ አማካሪዎች፣ከዚህ በፊት ከሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን ጋር ሠርተው፦
- የተሰጣቸውን ሥራ ቢያንስ 70% ያላጠናቀቁ ከባለሥልጣኑ የድጋፍ የምከር ደብዳቤ የሌላቸው፤ በቀደሙት የመንገድ ድልድይ ዲዛይን ሥራዎች የመጨረሻ ተቀባይነት (Final Acceptance) ያላስፈጸሙ እና የመጨረሻ ረቂቅ ሪፖርቶችን በSoft Copy እና Hand Copy ሙሉ በሙሉ እስከዚህ ጨረታ መዝጊያ ቀን ድረስ ያላስረከቡ፤በዚህ ጨረታ መሳተፍ አይችሉም።
8. በአንድ በላይ ሎት መሳተፍ አንድ ተጫራች በዚህ የመንገድ ዲዛይን አማካሪ አገልግሎት ከአንድ በላይ ሎት ላይ መሳተፍ አይችልም።
9. የባለሥልጣኑ መብት የሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን የጨረታውን ሂደት በከፊል ወይም በሙሉ የመቀበል ወይም የመሰረዝ መብቱን የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር፡- 0462 128 446/ሀዋሳ
ሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን
Tender details
- Deadline: 2026-10-31
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በኢትዮጵያ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ከ22ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-31 10:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በኢትዮጵያ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ከ22ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት
- Region: Sidama
- Publishing entity: Sidama Roads Authority
- Bid bond: 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር
- Bid document price: 1000.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published on: Addis Zemen (Oct 10, 2026)
- Posted at: 2026-10-10T08:33:48.000Z
- Source: Qelal Tenders