Products and Services
የጎፋ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የ2019 ዓም የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም የጎፋ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 የአውቶሞቲቭ ዲፓርትመንት እቃዎች 100,000ብር
- ሎት 2 የከተማ ግብርና ዲፓርትመንት እቃዎች 100,000ብር
- ሎት 3 የብረታ ብረት ዲፓርትመንት እቃዎች 100,000ብር
- ሎት 4 የኮምፒውተር ተጓዳኝ እቃዎች 100,000ብር
- ሎት 5 የኮንስትራክሽን ዲፓርትመንት እቃዎች 100,000ብር
- ሎት 6 የጋርመንት፤ ሌዘር እና ቴክስታይል ዲፓርትመንት እቃዎች 100,000 ብር
- ሎት 7 የፈርኒቸር ዲፓርትመንት እቃዎች 100,000 ብር
- ሎት 8 የሆቴል ዲፓርትመንት እቃዎች 100,000 ብር
- ሎት 9 አላቂ የጽዳት እቃዎች 100,000 ብር
- ሎት 10 የጽህፈት መሣሪያዎች 100,000ብር
- ሎት 11 የህትመት ስራዎች 50,000ብር
ከላይ ያሉትን የግዥ አይነቶች መሰረት በማድረግ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች
1. ለሚጫረቱበት ዘርፍ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው። የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው የሚገልጽ ማረጋገጫ፤ የቫትተመዝጋቢየሆኑናየምዝገባ ሰርተፊኬትእናበአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸው የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
2. የጨረታው ሰነድ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ ብር / በመክፈል ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 በኮሌጁ የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 4 በመቅረብ መውሰድ ይቻላል።
3.ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃ ኮሌጁ ባስቀመጠው ሎት መሰረት ለዘርፉ በአቅራቢነት መመዝገባችሁን በማረጋገጥ ዋጋቸውን በመሙላት የፅዳት እቃዎች እና ጽህፈትመሳሪያዎችላይ ብቻ በቅድሚያ ሳንፕል በማቅረብ በየሎቱ በፖስታ በማሸግና በግልፅ በመጻፍ ኦርጅናል ቴክኒካልና ፋይናንሻል እንዲሁም ቴክኒካልና ፋይናንሻል ፎቶ ኮፒ ሰርተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4.ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ (የቀን ብዛት 60/ ስልሳ ቀናት ብቻ ነው።
5.ዋጋ ሲሞላ በኮሌጁ ኦርጅናል ሰነድ ላይ መሆን አለበት።
6. ዋጋው ከነቫቱ መሞላት አለበት።
7.ጥቃቅንና አነስተኛ ተወዳዳሪዎች በጨረታ እንድትሳተፉ ከአደራጃችሁ ተቋም በኮሌጁ ስም ደብዳቤ መቅረብ አለባት።
8.ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከላይ በየሎቱ በተገለጸው መሰረት በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ ብቻ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
9.ተጫራቾች የጨረታ ውጤት በኮሌጁ ውስጥ ከተለጠፈ እና ደብዳቤ ከደረሳችሁ ቀን ጀምሮ ቅሬታ ካላችሁ በሰባት (7) ቀን ውስጥ በጽሁፍ መቅረብ አለበት።
10. በጨረታ አሸናፊ የሆነ ድርጅት ያሸነፈበትን ንብረት በራሱ የትራንስፖርት ወጭ በኮሌጁ ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርበታል።
11. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ11ኛው የስራ ቀናት 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ተዘግቶ በዛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ ላይብረሪ ይከፈታል። የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በስራ ቀን ያልዋለ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
12 .ኮሌጁ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ እንዲሁም ከቀረቡት ዝርዝሮች ውስጥ መርጦ የመግዛትና 20 ፐርሰንት ብዛት ለመጨመር ለመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡- ጥቃቅንን እና አነስተኛ ተደራጅታችሁ የምትወዳደሩ አቅራቢዎች በምታመርቱት ዘርፍ ወይም ለምታመርቱት ምርት ላይ 35% አድ ቫሊዩ ያለው መሆን አለበት ከዚህ ውጭ ኢምፖርት የተደረጉ ዕቃዎች ላይ ከተወዳደራችሁ እንደ መደበኛ ተጫራች ሲፒኦ ማሳያዝ ይጠበቅባችኋል እንዲሁምየጨረታ ሰነዱ ላይ የተቀመጡት ተግባራዊ እንዲደረጉ።
አድራሻ ጎፋ ካምፕ ወረዳ 5 ልዩ ስሙ የድሮ ገና ት/ቤት ከ20ቴ/ሙ/ማ/ተቋም በአሁኑ ጎፋ ኢንድስትሪያል ኮሌጅ
ስልክ ቁጥር፦ 011 470 4150 እና 011 466 6113/12
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ የጎፋ ኢንደስትሪያል ኮሌጅ
Tender details
- Deadline: 2026-10-22
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ11ኛው የስራ ቀናት 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-22 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ11ኛው የስራ ቀናት 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Gofa Industrial Collage
- Buyer address: ጎፋ ካምፕ ወረዳ 5 ልዩ ስሙ የድሮ ገና ት/ቤት ከ20ቴ/ሙ/ማ/ተቋም በአሁኑ ጎፋ ኢንዱስትሪያል
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ ብር/
- Published on: Addis Zemen (Oct 10, 2026)
- Posted at: 2026-10-10T09:06:31.000Z
- Source: Qelal Tenders