Catering and Cafeteria Services

ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ. አዲስ ካስገነባው 3B+G+25 ሕንጻ ላይ የሠራተኛ ካፍቴሪያ በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

Description

የሠራተኛ ካፍቴሪያ ሥራ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 01/2019

ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ. አዲስ ካስገነባው 3B+G+25 ሕንጻ ላይ የሠራተኛ ካፍቴሪያ በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

ተጫራቾች ማሟላት የሚጠበቅባቸው፡-

1. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና ብቁ ልምድ ያላቸው።

2. ተጫራቾች ስለ ጨረታው የሚገልፀውን ዝርዝር የጨረታ ሠነድ ከጥቅምት 3 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ ዋናው መ/ቤት ሀብት ሥራ አመራር መምሪያ(22ኛ ፎቅ) በመምጣት የማይመለስ ብር 400.00 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።

3. ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ብር 400,000.00 በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ከሚጫረቱበት ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4.ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የመጫረቻ ሰነድ እና ዋጋ በኤንቬሎፕ በማሸግ እስከ ጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ የኩባንያው ዋና መ/ቤት 22ኛ ፎቅ ላይ ለጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5. ጨረታው በዕለቱ ጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩባንያው ዋና መ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።

6. ኩባንያው ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡-

ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ ዋና መ/ቤት

ሀብት ሥራ አመራር መምሪያ (22ኛ ፎቅ)

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0910068772/0911430292 አዲስ አበባ።


Tender details

  • Deadline: 2026-10-23
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-10-23 14:15
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Nile Insurance Company S.C.
  • Bid bond: 400,000.00 ብር
  • Bid document price: 400.00 /አራት መቶ ብር/
  • Published on: Reporter (Oct 11, 2026)
  • Posted at: 2026-10-12T08:15:53.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders