Other
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ግልጽ የፕሮፖዛል መቀበያ ጥሪ ማስታወቂያ አውጥቷል
Description
ግልጽ የፕሮፖዛል መቀበያ ጥሪ ማስታወቂያ
በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 1113/2011 አንቀፅ 86 መሰረት በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን የሚተዳደር የሲቪል ማህበረሰብ ፈንድ እንደሚቋቋም ተደንግጋል። ባለስልጣን መስርያ ቤቱ ይህንኑ በሚመለከት ባወጣው የሲቪል ማህበረሰብ ፈንድ አስተዳደር መመርያ ቁጥር 848/2014 መሰረት በፈንዱ ተጠቃሚ የሚሆኑት በባለስልጣኑ ተመዝጋቢ ሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ብቻ ሲሆኑ የፈንዱም አላማ በጎ ፈቃደኝነት እና የዘርፉን እድገት ማበረታታት ፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድረጅቶችን ሀገራዊ አስተዋፅጾ ማበረታታት እና ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ዙርያ የሚሰሩ ድርጅቶችን ማበረታታትና ማገዝ ነው።
በመሆኑም ባለስልጣን መስረያ ቤታችን ከፈንዱ ድጋፍ ለማድረግ አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን ያጠናቀቀ ሲሆን በ2019 ዓ.ም ከፈንዱ የድጋፍ ከሚደረግበት የትኩረት ነጥቦች በልዩ ሁኔታ ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው የህ/ሰብ ክፍሎች ላይ የሚሰሩ እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሀገራዊ አስተዋጽኦ ማበረታታት ላይ የተለየ ትኩረት አድርገው ለሚሰሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የፋይናስ ድጋፍ ማድረግ ነው፡፡ በዚህመ መሰረት በተጠቀሱት የትኩርት ነጥቦች ላይ አሳማኝ እና ችግር ፈች የሆኑ ፕሮጀክት ፕሮፖዛሎችን ለሚያቀርቡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የፋይናንስ ድጋፍ ለማድረግ ይህንን ግልጽ የፕሮፖዛል መቀበያ ጥሪ ማስታወቂያ አውጥቷል።
ስለሆነም ለዚህ ግልጽ የፕሮፖዛል መቀበያ ጥሪ ማንኛውም ሀገር በቀል ድርጅት ከፈንዱ የፋይናንስ ድጋፍ ለማግኘት የሚያቀርባቸው ሰነዶች የሚከተሉት ዝርዝሮች የያዘ መሆን ይኖርበታል።
ሀ. የድርጅቱን ዝርዝር እቅድ የሚያሳይ የቴክኒክ እና የፋይናንስ ጉዳዮችን ያካተተ ፕሮጀክት ፕሮፖዛል
ለ. ማመልከቻውን ከሚያቀርበብበት አመት በፊት የተዘጋጀ አመታዊ የክንውን እና የፋይናንስ ሪፖርት
ሐ. በአንድ ድርጅት መቅረብ የሚችለው ፕሮጅክት ፕሮፖዛል አንድ ብቻ ሲሆን የፕሮጅክት መተግበሪያ ጣሪያ ስድስት ወር ግማሽ አመት/ መሆኑን በግልጽ በሚያሳይ መልክ ማስቀመጥ አለበት።
ሠ. ባለስልጣን መ/ቤቱ ለአንድ ፕሮጀክት ፕሮፖዛል ከፈንዱ ድጋፍ የሚያደርገው የገንዘብ ጣሪያ የምናሳውቅ ስለሆነ የሚቀርበው ፐሮጀክት ፕሮፖዛል አስተዳደራዊ እና አላማ ማስፈጸሚያ ወጭ ተካቶ የሚቀርብ ሆኖ በሚፈቀደው የገንዘብ መጠን ተሻሽሎ ይቀርባል።
ረ. የሚቀርበው ፕሮጀክት ፕሮፖዛል ይዘት ርዕስ፣ ማውጫ፣ መግቢያ፣ ዋናና ዝርዝር አላማወች፣ የማስፈጸሚያ ስልቶች፣ Risk mitigation Strategy, የሚጠበቁ ውጤቶች፣ የተግባራት ዝርዝር፣ የክትትልና ድጋፍ ስርዓት፣ የማብቂያ /የማስረከቢያ ስትራቴጂ፣ የፋይናንስና የሰው ኃይል እቅድ ያካተተና ከ15 ገጽ ያልበለጠ መሆን አለበት።
ተወዳዳሪዎች ይህ ግልጽ የፕሮፖዛል መቀበያ ጥሪ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር /10/ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከላይ የተዘረዘሩትን የመወዳደርያ ሰነዶች በማሟላት አዲስ አበባ አራዳ ክ/ ከተማ ቴዎድሮስ አደባበይ ከፍ ብሎ ሕብረት ኢንሹራንስ ህንጻ 6ተኛ ፎቅ ከሲ/ ማ/ድ/ፈንድ/አስ/ እና ን/ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈፃሚ ቢሮ ቁጥር 608 ማስረከብ አለባቸው፡፡ በአስረኛው የስራ ቀን የመወዳደርያ ሰነድ የሚገባው እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ ብቻ ይሆናል።
ማሳሰቢያ፡-
ባለሥልጣኑ ድጋፍ ለማድረግ የተሻለ መንገድ ካገኘ ማስታወቂያውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ እነደተጠበቀ ነው፤
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ በቁጥር 0115582437/0115582402 ይደውሉ።
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን
Tender details
- Deadline: 2026-10-22
- Bid closing time: 17:30
- Bid closing (note): ይህ ግልጽ የፕሮፖዛል መቀበያ ጥሪ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስረኛው የስራ ቀን 11፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-22 17:30
- Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰአት አልተገለፀም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Authority for Civil Society Organizations
- Published on: Addis Zemen (Oct 12, 2026)
- Posted at: 2026-10-13T07:43:52.000Z
- Source: Qelal Tenders