Service

በውሀ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የኮምቦልቻ ዋና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የጥበቃ አገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶች በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጥበቃ አገልግሎት ግዥ ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

WWC/KMCO/NCB 003/2019

በውሀ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የኮምቦልቻ ዋና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የጥበቃ አገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶች በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታ መሳተፍ ይችላሉ።

1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር አጠቃለው የከፈሉ ህጋዊና አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፣ የንግድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN No) ያላቸው።

2. ከፌዴራል ፖሊስ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ ከክልል የስራና ክህሎት ቢሮ የተሰጠ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሠረት ያደረገ የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ ያላቸው፣ ከተቋማት በዘርፉ የመልካም አፈፃፀም የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ የ2018 ዓ.ም የገቢዎች ኦዲት የተረጋገጠ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ የድርጅቱን አቅም የሚያሳይ የባንክ እስቴትመንት ማቅረብ የሚችሉ፣ የታደሰ በፍትህ ተቋማት የጸደቀ የቢሮ ኪራይ ውል ያላቸው፣ በጥበቃ ደህንነት ሥራው ተሰማርቶ ለመስራት ከመንግስት የፀጥታ መዋቅር ድጋፍ ያላቸው።

3. ተጫራቾች በተራ ቁጥር 1 እና 2 ላይ የተጠቀሱትን እና ሌሎቸ ተያያዥነት ያላቸውን የመልካም ስራ አፈፃፀም፣ የስራ ልምድ እና ሌሎች መረጃዎችን ኮፒ በማድረግ በመጫረቻ ሰነዳቸው ላይ ማካተት ይጠበቅባቸዋል።

4. የኮምቦልቻ ዋና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮዎች፣ እስቶሮች፣ ወርክሾፖች፣ የነዳጅ ማደያ፣ የጽ/ቤት ቢሮ ግንባታ፣ ማሽነሪዎች ተሽከርካሪዎች እና ኢኩፕመንቶች፣ የተለያዩ የግንባታ ግብዓቶችን በአጠቃለይ በ 20 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ሙሉ የዋና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ግቢ የሚጠብቁ ሲሆን በ15 /አስራ አምስት/ የጥበቃ ባለሙያዎች ለ አንድ ዓመት እያንዳንዱ የጥበቃ ባለሙያ በወር ለ 208 ሰዓት በቋሚነት የጥበቃ ስራውን የሚያከናውን ይሆናል።

5. ተጫራቾች በኮርፖሬሽናችን ስም የተዘጋጀ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) በሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና/ ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ የሚከፈል unconditional Bid Bond Guarantee/ ከጨረታ ዶክመንቱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6. ተጫራቾች መወዳደሪያ ሀሳባቸውን ማለትም የቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነዳቸውን በሁለት ቅጅዎች ዋና እና ኮፒ በማለት ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በተናጠል ለየብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማስገባት ይኖርበታል። ለቴክኒካል በተራ ቁጥር 1 እና 2 ላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች፣ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ እና ተያያዥ ሰነዶች በአንድ ፖስታ ማቅረብ እንዲሁም በሁለተኛው ፖስታ የፋይናንስ ሠነድ ለብቻ በማዘጋጀት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ኮምቦልቻ ዋና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 25 በአካል በመቅረብ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

7. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ የወጣበትን ቀን ጨምሮ በመቁጠር በ21ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ በ4፡30 በጽ/ቤቱ ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 25 ኮምቦልቻ ይከፈታል።

8. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር ብቻ) በጽ/ቤታችን ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ የሂሳብ ቁጥር 1000316177186 ገቢ በማድረግ በጽ/ቤታችን ኮምቦልቻ ከተማ ሸህሷቢር ቀበሌ ፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 4 ማግኘት ይችላሉ።

9. የጨረታው ውድድር በጥቅል የı/አንድ/ ዓመት የጥበቃ አገልግሎት ዋጋ ይሆናል።

10. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን 0335510805/0953281222 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

አድራሻችን፦ ኮምቦልቻ ሽህሷቢር ቀበሌ

በውሀ ስራዎች ኮርፖሬሽን የኮምቦልቻ ዋና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-02
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-02 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Water Works Corporation
  • Bid bond: 30,000.00 ብር
  • Bid document price: 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/
  • Published on: Addis Zemen (Oct 12, 2026)
  • Posted at: 2026-10-13T08:15:49.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders