Catering and Cafeteria Services

በወላይታ ዞን የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ የፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ የሚፈፀም ዓመታዊ መስተንግዶ እና ጽ/መሳርያ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ የጨረታ ማስታወቂያ

በ2019 የበጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ የሚፈፀም ዓመታዊ መስተንግዶ እና ጽ/መሳርያ ግዥ በደ/ኢ/ከ/መ በወላይታ ዞን የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ፋ/ፕ/ጽ/ቤት በኩል የሚከናወን ጨረታ ነው፡፡

  • ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የሥራ ንግድ ፈቃድ ያሳደሱ ፣ የቫትና የቲን ተመዝጋቢዎች ሲሆኑ ግዥ በምንፈጽመው በዕቃ ዓይነቶች የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ/ብር በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ገ/ቅ/ጽ/ቤት በመክፈል ሠነዱን ከቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ፋይ/ጽ/ቤት ግዥ ፋይ/ን/አስ/ር ሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 10 ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  • ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 20 በሥራ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ20ኛው ቀን ከቀኑ በ5፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ልክ በ5፡30 ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በይፋ ይከፈታል፡፡ 20ኛው ቀን በዓል ወይም ሰንበት ከሆነ በማግስቱ በተባለው ሰዓት ይከፈታል፡፡
  • በግዥ ፈጻሚ መ/ቤት በኩል በተዘጋጀው የጨረታ ስነድ ላይ ግልጽ ያልሆነ ነገር ካለ ጉዳዩን አስመልክቶ ለቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ጥያቄው በጽሑፍ ሲቀርብ ማብራሪያ ይሰጣል ፡፡
  • የመጫረቻ ሀሳብ በመ/ቤታችን በኩል ተዘጋጅቶ በሚቀርብ መደበኛ የጨረታ ሠነድ እንጂ በሌላ መንገድ/ዓላማ በተዘጋጀ ሰነድ የመወዳደሪያ ሀሳባቸውን ማቅረብ አይፈቀድም ::
  • ጨረታው የሚስተናገድበት ቋንቋ የሀገሪቱ የሥራ ቋንቋ በሆነው አማርኛ ቋንቋ ይስተናገዳል፡፡
  • የጨረታ ግምገማ በጋዜጣ በተገለጸው መሠረት የጨረታ ማወዳደሪያ ዘዴው በጥቅል ዝቅተኛ ዋጋን መሠረት በማድረግ የሚፈፀም በመሆኑ የእያንዳንዱ የጽ/መሳሪያ እና የመስተንግዶ ዓይነት ዋጋ መመዝገብ ይጠበቅበታል ፡፡
  • ከጨረታው ጋር በተያያዘ ሂደቱን ለማዛባት የሚፈፀሙ ማንኛውም ዓይነት ህገ-ወጥ ድርጊቶች በህግ ከማስጠየቁ ሌላ ከተወዳዳሪነት ውጭ ያደርጋል፡፡
  • በጨረታ ሰነዱ ላይ የተቀመጡ ዕቃግዥ ከተፈፀሙ በኋላ ለመንግሥትና ለህዝብ በትክክል አገልግሎት የሚሰጡ ጥራት ያላቸውና ጥራታቸው የተረጋገጠ ስለመሆኑ በውሉ ውስጥ ይካተታል፡፡
  • ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሠድ ተቀባይነት አይኖረውም ፡፡
  • በዋጋ አቅርቦት ወቅት ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ተወዳዳሪዎች እኩል ዋጋ ያቀረቡ ከሆነ አሸናፊውን ተጫራች ለመለየት ሌላ የማወዳደሪያ ሀሳብ እንዲያቀርቡ/በዕጣ የመለየት የተጫራቾቹ ስምምነት ተጠይቆ ተፈጻሚ ይደረጋል፡፡
  • የጽ/መሳሪያ እና የመስተንግዶ ጨረታ ዋጋ ጨረታው ይፋ ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ ለአንድ ዓመት ተከታታይ ፀንቶ ይቆያል፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 10000 /አስር ሺህ ብር/ ለመስተንግዶ 25000/ሃያ አምስት ሺህ ብር/ ጽ/መሳርያ በባንክ የተረጋገጠ CPO፣ በጥሬ ገንዘብ እና ለቴር ኦፍ ክሬዲት ማስያዝ አለባቸው፡፡
  • ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ የግዥው 10% በባንክ የተረጋገጠ CPO ፣ በጥሬ ገንዘብ እና ለቴር ኦፍ ክሬዲት ማስያዝ አለባቸው፡፡
  • የጨረታውን አስፈላጊ ሠነዶች የያዘ ፖስታ ዋናና ኮፒ በታሸገ ኤምቬሎፕ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
  • ለመጫረት የሚያቀርቡት ማንኛውም ዓይነት ሠነዶች ህጋዊ ሥልጣን ባለው አካል የተፈረሙ ማህተም ያረፈባቸውና ለውድድሩ አስፈላጊ ናቸው የተባሉ ሰዶች በሙሉ ህጋዊነታቸው የተረጋገጠ መሆን አለበት ፡፡
  • በጨረታው ሂደት ላይ ቅሬታ ካለዎት በግዥ አዋጅ ምዕራፍ 14 አንቀጽ 44 እና 46 መሠረት አቤቱታ ማቅረብ ይቻላል ፡፡
  • የጽ/መሳሪያ ናሙና ተጫራቾች የሚያቀርቡት ይሆናል፡፡
  • መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካለው ጨረታውን እንደአስፈላጊነቱ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0910 503 789፣ 0916 684 480 ወይም 0910 464 702 ይጠቀሙ

በወላይታ ዞን የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ የፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-04
  • Bid closing time: 11:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 20 በሥራ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ20ኛው ቀን ከቀኑ በ5፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-04 11:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 20 በሥራ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ20ኛው ቀን ከቀኑ በ5፡30 ሰዓት
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: Boloso Sore Woreda Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 12, 2026)
  • Posted at: 2026-10-13T08:50:30.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders