Contract Administration and Supervision

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የኢትዮጵያን አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎችና ሰራተኞች ካፍቴሪያ ህንፃ ማስፋፊያ ፕሮጀከት የንድፍ ከለሳ፣ የኮንትራት አስተዳደር እና የግንባታ ክትትል የማማከር አገልግሎት (Design Review Construction Supervision & Contract Administration Service for Ethiopian Aviation University (EAU) Students and

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር: -SSNT-T649

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ብቁ የሆኑ ደረጃ አንድ (1) እና ከዚያ በላይ የሃገር ውስጥ ጨረታ ለመሳተፍ ፈቃድ ያላቸው የሃገር ውስጥ እና አለም አቀፍ አማካሪ ድርጅቶችን የኢትዮጵያን አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎችና ሰራተኞች ካፍቴሪያ ህንፃ ማስፋፊያ ፕሮጀከት የንድፍ ከለሳ፣ የኮንትራት አስተዳደር እና የግንባታ ክትትል የማማከር አገልግሎት (Design Review Construction Supervision & Contract Administration Service for Ethiopian Aviation University (EAU) Students and Staff Cafeteria Expansion consultancy service) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

ስለሆነም ለስራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣ በዘርፉ ለመሰማራት የሚያስችል የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ ከሚሰጥ ህጋዊ አካል የታደሰ ደረጃ 1 ወይም ከዚያ በላይ የሆነ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣ የግብር ከፋይ መለያ ሰርተፊኬት (TIN)፣ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ የሚያገለግል ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ ጨረታውን እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 200.00 ብር (ሁለት መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T649 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጅ (Deposit Slip Copy)፣ የጨረታውን ቁጥርና አይነት እንዲሁም የድርጅቱን ሙሉ አድራሻ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ።

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሁለት መቶ ሺህ ብር (200,000.00) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ከማንኛውም ኢንሹራንስ ተቛም እና ቅድመ ሁኔታ ያለው የባንክ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።

ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ጀምሮ ለ150 ቀናት የሚቆይ ይሆናል። አየር መንገዱ ጨረታው የሚቆይበትን ጊዜ እንዲራዘምለት ተጫራቾችን የመጠየቅ መብት አለው።

የፕሮጀክቱ ማጠናቀቂያ ጊዜ የንድፍ ክለሳ/Design review 60 ተከታታይ ቀናትን ጨምሮ ሥራው ከተጀመረበት ቀን ጀምሮ 270 ተከታታይ ቀናት ውስጥ መጠናቀቅ አለበት። ፕሮጀክቱ የሚገኘው በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በሚገኘው የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ነው።

ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጨረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ በኤንቨሎፕ አሽገው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል  ጥቅምት 26/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መሥሪያ ቤት የጨረታ መከፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ በ 9:00 ሰዓት ይከፈታል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ: የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ

ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል

ስልክ ቁጥር፡ 011-517-8025

ኢ-ሜይል: [email protected] 

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

Ethiopian

የኢትዮጵያ


Tender details

  • Deadline: 2026-11-05
  • Bid closing time: 14:30
  • Bid opening: 2026-11-05 15:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Airlines Group (ETG)
  • Buyer TIN: 0000028498
  • Bid bond: 200,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 12, 2026)
  • Posted at: 2026-10-13T09:30:15.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders