Chemicals and Reagents
በአራዳ/ክ/ከ/ወ/2 የስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ በ2019 የበጀት ዓመት በሎት ከፋፍሎ ለማጫረት ይፈልጋል
More tags
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ማስታወቂያ ቁጥር ስ/ከ/ጤ/ጣ/01/2019
በአራዳ/ክ/ከ/ወ/2 የስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ በ2019 የበጀት ዓመት በሎት ከፋፍሎ ለማጫረት ይፈልጋል።
- ሎት 1 የተለያዩ ቋሚ እቃዎች፣ መዳኒቶችና የላብራቶሪ ሬጀንቶች
- ሎት 2 የተለያዩ የጽዳት እቃዎች፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የደንብ ልብስ ጨርቆችና ጫማዎች ፣ ህንጻ፣ ለቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚዎች እድሳት እና ጥገና ግብዓት እቃዎች፣ ህትመቶች፣ የመኪና ጐማና መለዋወጫ
- ሎት 3. የውሃ ታንከር ፅዳት አገልግሎት፣ የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት የሚሰጡ፣ የጭነት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከሪካሪዎች፣ የጀነሬተር ጥገና አገልግሎት የሚሰጡ፣ የአይቲ ጥገና አገልግሎት የሚሰጡ፣ የለስላሣ አቅርቦትና መስተንግዶ አገልግሎት የሚሰጡ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ፡-
1. ከሚገዛው ዕቃ /አገልግሎት/ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ የዘመኑ ንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/Tin No/ ማቅረብ የሚችሉ፣
2. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚገልፅ የምዝገባ የምስክር ወረቀት /በዌብሳይት የተመዘገቡ ተጫራቾች ከዊብሳይቱ ላይ ኘሪንት አድርገው ማቅረብ የሚችሉ።
3. ተጫራቾች በየዘርፉ የተወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ከ50 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
4. ተጫራቾች በተወዳደሩበት ሎት ላይ የጨረታ ሰነድ ማስከበሪያ 2% ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) በባንክ በተረጋገጠ በጤና ጣቢያው ስም ማቅረብ የሚገባቸው ሲሆን የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይሆናል።
5. ተቋማችን የሚገዛቸውን የአገልግሎት/ የዕቃዎች አይነት ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ውስጥ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን በየሎቱ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 150 በመክፈል በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ስመኝ ከበደጤና ጣቢያ 3ኛ ፎቅ ፋይናንስ ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ፓስታ ለዚሁ አገልግሎት ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ ግዥ ቢሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ቫትን ያላካተተ፣ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም አድርጐ የማያቀርብ፣ ስርዝ ድልዝ ያደረገ እና አማራጭ ጨረታ የተጠቀሙ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም።
8. የጨረታው ሣጥን በአስራ አንደኛው ቀን 3፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን በ3፡30 ሰዓት ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ አዳራሽ ጨረታው በግልጽ ይከፈታል።
9. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የደንብ ልብሶች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ ህንጻ፣ለቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚዎች እድሳት እና ጥገና ግብዓት እቃዎች ጥራት ለመለየት የሚያስችል ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ ከአንድ ቀን በፊት በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ ግዥ ቢሮ ገቢ ማድረግ አለባቸው። ናሙና ያላቀረበ ተወዳዳሪ ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል።
10. በቋሚ እቃዎች ላይ የሚጫረቱ ተጫራቾች ከሰነዳቸው ጋር የፎቶና እስፔስፊኬሽን ማቅረብ አለባቸው ፎቶ እስፔስፊኬሽን ያላቀረበ ተወዳዳሪ ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል።
11. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈውን እቃ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ ጤናጣቢያው እቃ ግምጃ ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
12. መ/ቤቱ እንደ አስፈላጊነቱ 20% /ሀያ ከመቶ/ጨምሮ ወይም ቀንሶ መግዛት ይችላል።
13. መ/ቤቱ የተሸለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፦ በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ ከራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል አለፍ ብሎ ታደሰ ቸኮል ኮሜርሻል 100 ሜትር ገባ ብሎ ወረዳ 2 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ +251 11 126 53 33/ 09 11 44 12 57 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።
በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ
Tender details
- Deadline: 2026-10-24
- Bid closing time: 09:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው ቀን 3፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-24 09:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው ቀን 3፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Simegn Kebede Health Post
- Buyer address: በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ ከራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል አለፍ ብሎ ታደሰ ቸኮል ኮሜርሻል 10 ሜትር ገባ ብሎ ወረዳ 2 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 150.00 /አንድ መቶ ሀምሳ ብር/ ለእያንዳንዱ ሎት
- Published on: Addis Zemen (Oct 13, 2026)
- Posted at: 2026-10-13T11:20:14.000Z
- Source: Qelal Tenders