Generators
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት የተለያዩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
Description
ጀነሬተሮች እና የተለያዩ ተሽከርካሪዎች ግዥ ግልጽ ጨረታ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር የኮ/ዲ/ግ/ማ/ድ/ግ/ጨ/ቁ 06/2018
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት ከዚህ በታች በሎት ተከፋፍሎ በተቀመጠው መሰረት በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
- ሎት 1፡- ጀነሬተሮች
- ሎት 2፡- የኤሌክትሪክ አውቶሞቢሎች
- ሎት 3፡- ከባድ መኪኖች
ስለሆነም ፡-
1. በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል በዘርፉ የተሰጠ የታደሠ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፤ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ኮፒ አያይዘዉ ማቅረብ የሚችሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ እና በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ድርጅቶችና ግለሰቦች የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) ብር በመክፈል በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ግንባታና ማማከር ድርጅት ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ መግዛት ይችላሉ።
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 ብር 60,000.00 (ስልሳ ሺህ ብር) ለሎት 2 ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) ለሎት 3 ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የ90 ቀናት የባንክ ዋስትና (unconditional bid bond guarantee) ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
3. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከረፋዱ 5፡00 ሰአት ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
4. የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ግንባታና ማማከር ድርጅት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ
ስልክ ቁጥር 09-13-56-49-36 / 09-11-15-60-26
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-10-31
- Bid closing time: 10:30
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰአት
- Bid opening: 2026-10-31 11:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 5፡00 ሰአት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ababa Administration Construction Design, Building and Consultancy Organization
- Buyer address: አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 14, 2026)
- Posted at: 2026-10-14T10:24:09.000Z
- Source: Qelal Tenders