Chemicals and Reagents

በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ጽሕፈት ቤት የተለያዩ ለፋብሪካ አገልግሎት የሚውሉ የፋብሪካ ኬሚካሎችን (Factory Chemical) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት የወጣ ማስታወቂያ (የጨረታ ቁጥር LP/OT/004/OKSF1&3/2019)

Description

ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- LP/OT/004/OKSF1&3/2019

በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ጽ/ቤት የተለያዩ ለፋብሪካ አገልግሎት የሚውሉ የFactory Chemical ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሰነድ ጋር ህጋዊ የታደሰ አዲስ የንግድ ፈቃድ የዘመኑን ግብር መከፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፤ በተጨማሪም ተጫራቾች የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አጀንሲ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ መረጃ ማቅረብ አለባቸው ::
  2. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከሚመለከተው አድራሻ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ አስከ ዓርብ ከሰዓት በፊት ከ2፡30-6፡00፣ ከሰዓት ከ7፡00-6፡30 እና ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ከ2፡30-6፡00) ቀጥሎ ከተመለከተው አድራሻ በመቅረብ ገዝተው በጫረታው መሳተፍ ይችላሉ፡

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ

የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ

ግዥ ቡድን (ማስተባበር ቢሮ)

አድራሻ፡- ኮልፌ ቀራኒዮ፣

ከጦር ሃይሎች ወደ ዘነብ ወርቅ በሚወስደው መንገድ

በተለምዶ 3 ቁጥር ማዞሪያ / ቶታል ገባ ብሎ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ህንፃ ላይ

ሕ - 8 ቢሮ ቁጥር 1371/125 ፎቅ

የስልክ ቁጥር (አድራሻ) +251-963442882/+251913544731/+251-916170834

አዲስ አበባ

3.ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው የፋብሪካ ኬሚካሎች የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይም በቅድመ ሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ከመጫረቻ ስነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::

4.ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው 16/02/2019 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን 16/02/2019 ዓ.ም 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፡፡

5. ጨረታው ዋጋ ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ30 ቀናት ነው፡፡

6.የጨረታው ማስረከቢያ ዋስትና ፀንቶ የመቆያ ጊዜ ለ 60 ቀናት ነው፡፡ ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-26
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-10-26 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Sugar Industry Group
  • Buyer address: ካሳንቺስ ፣ ከንግድ ሚኒስቴር በስተቀኝ ገባ ብሎ ጆሴፍ ቲቶ መንገድ ከኪያሜድ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ሕንፃ በስተጀርባ የሚገኘው 4ኛ ፎቅ ላይ
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 15, 2026)
  • Posted at: 2026-10-15T08:26:06.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders