Animal Feed

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ እንስሳት ምርምር እና እርባታ ማዕከል ለ2018 ዓ.ም. የሚውሉ ለእንስሳት መኖነት የሚያገለግሉ የድርቆሽ ሳር እና ጭድ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቀያ

የጨረታ ቁጥር እ/ህ/ግ/ኮ 002/2019

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ እንስሳት ምርምር እና እርባታ ማዕከል የ2018 ዓ.ም

  • ለእንሰሳት መኖነት የሚገለግሉ የድርቆሽ ሳር እና ጭድ ግዥ የወጣ ግልጽ ጨረታ ነው።

ስለሆነም፡-

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸው እንዲሁም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  2. ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለሥልጣንየተሰጠ ማስረጃ የታክስ ከፋይ (Tin No) የምስክር ወረቀት፤ የአቅራቢዎች ምዝገባ/supplier list/ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችለ መሆን አለባቸው።
  3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር (80,000.00) ሰማኒያ ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ወይም የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው ።
  4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00/ አምስት መቶ ብር/ በመክፈል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው የእንሰሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ ግዥ ክፍል በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን የያዘውን ሰነድ አንድ ቴክኒካል ኦሪጂናልና አንድ ቴክኒካል ኮፒ እና አንድ ፋይናንሽያል ኦርጅናልና አንድ ፋይናንሽያል ኮፒ በእናት ፖስታ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ 16ኛው ቀን 7፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በኮሌጁ ግዥ ክፍል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
  6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን በ7፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ8፡00 ሰአት በግልጽ ይከፈታል። የመክፈቻ ቀኑ የሕዝብ በዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው መዝጊያ ሰዓት ታሽጎ በግልጽ ይከፈታል።
  7. በጨረታ መክፈቻ ቀኑ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አይስተጓጎልም።
  8. ተጫራቾች የአሸነፏቸውን አቅርቦቶች በሚሰጣቸው ትዕዛዝ መሰረት በቢሾፍቱ ከተማ የእንስሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ በራሳቸው  ትራንስፖርት  በማጓጓዝ ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
  9. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር 011 433 8557/ 09 13 07 96 97

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንሰሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ

ቢሾፍቱ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-30
  • Bid closing time: 13:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ7፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-30 14:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንሰሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ
  • Bid bond: 80,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 15, 2026)
  • Posted at: 2026-10-15T10:01:17.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders