Health Related Services and Materials

የአ/ከ/ክ/ከተማ ወረዳ 3 ጤና ጣቢያ የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የአ/ከ/ክ/ከተማ ወረዳ 3 ጤና ጣቢያ ለ 2019 በጀት ዓ.ም ለሁለተኛ ዙር የወጣ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ እና ውል መፈፀም ይፈልጋል፤

የዚህም ጨረታ የገንዘብ ምንጭ የመንግስት ግምጃ ቤት እና የውስጥ ገቢ ነው።

በዚህ መሰረት ተጫራቾች፡-

  • ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
  • የዘመኑን ግብር የከፈሉ
  • በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል እንዲሁም በጥቃቅን እና አነስተኛ የምትወዳደሩ ተጫራቾች ከአደራጃችሁ ተቋም የአምራችነት ደብዳቤ በማምጣት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር(10) ተከታታይ የስራ ቀናት ጤና ጣቢያዉ ቅጥር ግቢ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 411 የጨረታ ሰነዱን በመውሰድ የሚወዳደሩበትን የጨረታ ዋጋ ሰነዱ ውስጥ በሚገኝ የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር መሰረት ከነቫቱ ሞልተው ያስገባሉ።

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ፡-

  • ሎት 1. የሰው መድሃኒት እና የህክምና እቃዎች ግዥ ከተበጀተው 0.3%) 66,000.00 ብር
  • ሎት 2. የጥገና እና ግንባታ ስራዎች ግዥ ከተበጀተው 2%)50,000.00 ብር
  • ሎት 3. የኮምፒውተር ጥገና ስራዎች ግዥ ከተበጀተው 0.5%)10,000.00 ብር

ተጫራቾች ያሸነፉበትን የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ በተመሰከረ የክፍያ ትዕዛዝ | ሲ.ፒ.ኦ / በጤና ጣቢያው ስም ተሰርቶ መቅረብ ይኖርበታል ፤ተጫራቾች ሙሉ ሰነዱ ላይ ፊርማ እና ማህተም ተደርጎ በተጫራች የሚሞሉትን ክፍሎች ተሞልተው ሰነዱ ተፈርሞበትና የድርጅቱ ማህተም ተደረጎበት ይመለሳል፤ለጥቃቅን ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ ደብዳቤ ከአደራጃችሁ ተቋም ማምጣት ይኖርባችሁዋል።

ሙሉ ሰነዱ ላይ ፊርማ እና ማህተም ተደርጎ በተጫራች መሞላት ያለባቸው ክፍሎች ተሞልተው የህክምና እቃዎች መገለጫ /እስፔስፍኬሽን/ እንዲሁም ካታሎግ ለብቻው በአንድ ታ ፖስታ የሚደረግ ሲሆን መደበኛ የጨረታ ሰነዱ ኮፒ ተደረጎ ከዋናው ሰነድ ጋር ሲፒኦውን ማስገባት እና መመለስ ይጠበቅባቸዋል፡፡ጨረታዉ በ10ኛው ቀን እስከ 11፡30 ድረስ ተጫራቾች ሰነዳቸውን ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በ11ኛው ቀን ጠዋቱ 3፡30 ተዘግቶ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጤና ጣቢያዉ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፤ በማንኛውም ምክንያት ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይሆናል ፡፡መ/ቤቱ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ በ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ ከኮካ አደባባይ ወደመሣለሚያ ወይም ከመሣለሚያ ወደ ኮካ አደባባይ በሚሄደው ዋና መንገድ ሲሄዱ የቀድሞ 24 ቀበሌ መዝናኛ ክበብ ፊት ለፊት ባለው ዳገታማ መንገድ 200 ሜትር እንደሄዱ በሚታየው ባለ አራት ፎቅ ህንፃላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ፡-በስልክ ቁጥር 0118-27-56-08 ወይም 0118-27-90-60 /

ማሣሰቢያ

ጥብቅ ማሳሰብያ፡- የህክምና መገልገያ መሳርያዎችላይየምትወዳደሩ ተጫራቾች የምትወዳደሩበትን ዋጋ ሞልታችሁ የምታስገቡት የመድሃኒት ዋጋ ከሞላችሁበት ጋር ሳይሆን የህክምና እቃዎችን የሞላችሁበትን ፖስታውን ከተቋሙ የምትወስዱትን የጥራት እስፔስፍኬሽን ጋር በማድረግ

  • ማንኛውም ተጫራች እስፔስፊኬሽን / የጥራት ልዩ መግለጫ  እቃውን ከመገጠሙ በፊት ለባለሙያ እና ለጥራት ኮሚቴ አሳይቶ መገጠም ያለበት መሆኑን እንገልፃለን።
  • የሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ሁሉ ከቫት ጋራ የተሰላ ተጨማሪ እሴት ታክስን ያከተተ መሆን ይኖርበታል፡፡ ከቫት ጋራ ያልተሰላ/ተጨማሪ እሴት ታክስን ያላከተተ ከሆነ ለአሠራራችን አመቺ ስለማይሆን ለውድድር አናቀርበውም።

የአ/ከ/ክ/ከተማ ወረዳ 3 ጤና ጣቢያ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-30
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ጠዋቱ 3፡30
  • Bid opening: 2026-10-30 10:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ጠዋቱ 4፡00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ketema Sub City Wereda 3 Health Post
  • Buyer address: ከኮካኮላ አደባባይ ወደ መሣለሚያ ወይም ከመሣለሚያ ወደ ኮካኮላ አደባባይ በሚወስደው ዋና መንገድ ሲሄዱ የቀድሞ 24 ቀበሌ መዝናኛ ክበብ ፊት ለፊት ባለው ዳገታማ መንገድ 200 ሜትር እንደሄዱ በሚታየው ባለ 4 ፎቅ ህንፃ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Oct 18, 2026)
  • Posted at: 2026-10-19T08:30:55.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders