Products and Services
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የቃሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የአትክልት ዘር /ማንጎና አቮካዶ/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የቃሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ን/አስ ቡድን ለቃሉ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል ጥራት ያለው የአትክልት ዘር /ማንጎና አቮካዶ/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በጨረታ መለያ ቁጥር ፡ቃ/ወ/ግ/ጨ |006/2019
- ተጫራቾች ኦርጂናል በዘመኑ የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግዥው መጠን ከብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ክፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀትና እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች ማቅረብ ሲጠበቅባቸው የመረጃወቹ የማይመለስ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ መታሸግ ይኖርበታል።
- የአትክልት ዘሩን በተመለከት ቢሮአችን በሚገኝበት ኮ/ቻ ከተማ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ሲኖርባቸው ዘሮቹን ንብረት ክፍል ድረስ የማስገባትና እንዲሁም ሌሎች ወጭዎችን የሚሸፍነው አቅራቢው ድርጅት ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ግብር የከፈሉበትን ህጋዊ መረጃ ማቅረብ አለበት፡፡
- የሚፈለገውን እቃና አገልግሎት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት 11፡30 ሰዓት ድረስ ቃሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 9 በመምጣት የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በጥሬ ገንዘብ በመክፈል መግዛት ትችላላችሁ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ዋናና ኮፒ በማለት ለየብቻ በፖስታ አሽጎ ስምና አድራሻውን በመጻፍ ቃሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 06 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመቁጠር 11ኛው ቀን ከጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ፖስታውን ማስገባት የሚችል ሲሆን በዚሁ እለት 4:00 ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የሌለው ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በመክፈቻው እለት የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም፡፡
- ለእቃ ግዥ ከብር 20,000 በላይና ለአገልግሎት ግዥ ከብር 10,000 ብር በላይ ዋጋ ከተሞላ ከሚከፈለው ክፍያ ላይ 3% የቅድመ ግብር ተቀንሶ የሚቀር መሆኑ ይታወቅ
- ማንኛውም ተጫራች የሞላውን ዋጋ ብዜት ወደ ጎን እንዲሁም ጠቅላላ ድምሩን ወደታች ካላስቀመጠ፤ በነጠላም ሆነ በጠቅላላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለና በንባብ በተሰማው ጠቅላላ ዋጋና በሚመለከተው አካል ተሰልቶ በሚገኘው ጠቅላላ ዋጋ መካከል ከ3% በላይ ልዩነት ካለ ተጫራቹ ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ለ73/ሰባ ሶስት ተከታታይ ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ሲሆን የመጫረቻ ሰነዱ ደግሞ ጨረታው ከሚከፈትበት እለት ጀምሮ ለ45 አርባ አምስት) ተከታታይ ቀናት ጸንቶ ይቆያል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 60,000 (ስልሳ ሺ ብር ብቻ በሲፒአ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው፡፡ የሚያስይዙት የጨረታ ማስከበሪያ በቢድ ቦንድ ከሆነ ከ73 ቀን ያነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ካሉት 5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት ተከታታይ ቀናት ውስጥ የጠቅላላ ዋጋውን 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል የመውሰድ ግዴታ አለበት፡፡
- የጨረታ መከፈቻ ቀኑ የበአል ቀን ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰኣት ይከፈታል፡፡
- ውድድሩ የሚካሄደው በሎት ድምር ነው :
- አሸናፊው ተወዳዳሪ ጥራት ያለው የአትከልት ዘር አማራ ክልል ቃሉ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ድረስ የማቅረብ ግዴታ ያለበት ሲሆን ገቢ የሚደረገው በሚመለከተው ባለሙያ ጥራቱ ከተረጋገጠ በኋላ ነው፡፡
- መ/ቤቱ ከአሸናፊው ድርጅት ወይም ግለሰብ ከአሸነፈው እቃ መጠን ላይ 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው::
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ማግኘት ከፈለጉ ቃሉ ወረዳ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 06 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0335514644 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
በአብክመ ደ/ወሎ ዞን የቃሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን
Tender details
- Deadline: 2026-10-28
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋት 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-28 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋት 4፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: ANRS Kalu Woreda Finance and Economic Development Bureau
- Bid bond: 60,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 18, 2026)
- Posted at: 2026-10-19T08:56:29.000Z
- Source: Qelal Tenders