Products and Services

የአማራ ክልል ስቴት ዩኒቨርሲቲ የወፍጮ አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ማስፈጨት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 03/2019

የአማራ ክልል ስቴት ዩኒቨርሲቲ ለ2019 በጀት ዓመት ለስልጠና አገልግሎት የሚውል

  • ሎት 1. የወፍጮ አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ማስፈጨት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
  2.  የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው።
  3.  ከመንግስት የሚጠበቅባቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  4. የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  6.  ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በየሎቱ በመክፈል በዩኒቨርሲቲው ግቢ ቢሮ ቁጥር 19 መግዛት ይችላሉ፡።
  7.  የሚገዙ የዕቃዎችን አገልግሎቶችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
  8. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለጽ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከጥቅምት 09/2019 ዓ/ም ጀምሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በዩኒቨርሲቲው የግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 19 ማስገባት ይችላሉ።
  9.  ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ሎት በጨረታ ሰነዱ የተገለፀውን የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው።
  10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ወጥ በሆነ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ በዩኒቨርሲቲው ግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ወይም ቢሮ ቁጥር 19 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጥቅምት 09/2019 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 18/2019 ዓ.ም 9፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  11. የጨረታ ሳጥኑ ጥቅምት 18/2019 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዩኒቨርሲቲው አዳራሽ ይከፈታል።
  12. የመክፈቻው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  13. ዩኒቨርስቲው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  14. በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለዉም።
  15. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 19 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 23 60 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

የአማራ ክልል ስቴት ዩኒቨርሲቲ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-28
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-10-28 10:30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Amhara Regional State University
  • Bid document price: 500.00 ብር በየሎቱ
  • Published on: Be'kur (Oct 19, 2026)
  • Posted at: 2026-10-19T13:41:39.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders