Vehicles Purchase
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ለድርጅቱ አገልግሎት የሚውሉ ፕክአፕ እና የኤሌክትሪክ ሚኒ-ባስ ተሽከርካሪዎች ግዥ ከተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCDE 002/2019
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ለድርጅቱ አገልግሎት የሚውሉ ፕክአፕ እና የኤሌክትሪክ ሚኒ-ባስ ተሸከርካሪዎች ግዥ ከተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
በዚህም መሰረት፡-
- ማንኛውም ተጫራች ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን እና የታክስ ክፍያ መለያ ቁጥር (TIN) የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ ስለመሆናቸው በግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ታክስ ክሊራንስ፣የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣የውጪ አገር ተጫራቾች በሚሆኑበት ጊዜ በተቋቋሙበት አገር የተሰጣቸውን የኩባንያ ምዝገባ ወረቀት ወይም ፈቃድ፣የአገር ውስጥ አምራች ወይም ገጣጣሚ ወይም የአምራች ህጋዊ ወኪል ማስረጃ(letter of authorization) የገጣጣሚ ህጋዊ ፈቃድ ወዘተ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱ በድርጅታችን ፋይናንስ ዴስክ መውሰድ ይጠበቅባችኋል::
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በIOR በተያያዘው ዝርዝር መሠረት መሆን ይኖርበታል::
- ጨረታው ከጥቅምት 8 ቀን 2019 እስከ ጥቅምት 23 ቀን 2019 ዓ.ም አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ጥቅምት 23 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ይካሄዳል:: ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዢ ዴስክ ይከፈታል:: ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በአከፋፈት ሂደት ባይገኙም የጨረታው የአከፋፈት ሂደት አያግደውም::
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ከላይ በተገለፀው ቀንና ሰዓት በድርጅቱ የግዥ ዴስክ አራተኛ ፎቅ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ድርጅታችን ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እሁድ ወይም የህዝብ በአል ቀን ከሆነ ቀጣይ ወዳለው የስራ ቀን ይተላለፋል::
- የጨረታ ማስከበሪያ እንደ ተጫራቹ ምርጫ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ወይም በባንክ የተሰጠ የተረጋገጠ ቼክ(CPO) ብር 432,000.00(አራት መቶ ሰላሳ ሁለት ሺ ብር) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡
አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 011 5570640
አድራሻ ካሳንቺስ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጀርባ ከዚህ ቀደም ስኳር ኮርፖሬሽን የነበረበት የኪያ-ሜድ ኮሌጅ ህንጻ አራተኛ ፎቅ
Tender details
- Deadline: 2026-11-02
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-11-02 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Defence Construction Design Enterprise
- Buyer's registered address: ወሎ ሰፈር አምባሰል ህንፃ ፊት ለፊት የቀድሞው ኖሬላ ግቢ ውስጥ
- Bid bond: 432,000.00(አራት መቶ ሰላሳ ሁለት ሺ ብር)
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Reporter (Oct 18, 2026)
- Posted at: 2026-10-20T07:25:28.000Z
- Source: Qelal Tenders