Vehicles Purchase
የወጣት ሴቶች ክርስቲያናዊ ማህበር በኢትዮጵያ (YWCA in Ethiopia) በነዳጅ የሚሰራ ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው ተሽከርካሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ ጨረታ
የወጣት ሴቶች ክርስቲያናዊ ማህበር በኢትዮጵያ
(YWCA in Ethiopia)
የወጣት ሴቶች ክርስቲያናዊ ማህበር በኢትዮጵያ (YWCA in Ethiopia) አለማቀፋዊ ይዘት ያለው፣ በበጎ ፈቃደኝነት የሚንቀሳቀስ መንግሥታዊ ያልሆነ ማህበር ነው። ማህበሩ የዘርም ሆነ የሃይማኖት ልዩነት ሳያደርግ መልካም ስብዕና ያላቸውና በበጎ ሥነ-ምግባር የታነፁ ዜጎችን ለማፍራት፣ እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን፣ በተለይም ወጣት ሴቶችን አቅም ለማጎልበት በፌዴራል የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ በቁጥር 0237 ተመዝግቦ የሚንቀሳቀስ ሀገር በቀል ድርጅት ነው፡፡
ድርጅቱም በነዳጅ የሚሰራ ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው ተሽከርካሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም ይህን ጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች ከጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በቢሮው በመገኘት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን ማቅረብ ይችላሉ፡፡
የተሽከርካሪው ቴክኒካዊ መስፈርቶች
- የመኪና አይነት፦......በነዳጅ የሚሰራ ተሽከርካሪ
- ተመራጭ ሞዴል፦ Suzuki Alto ወይም ተመጣጣኝ ሌላ ሞዴል
- የሞዴል ዓመት፦...20222025
- የሞተር አቅም፦..1000 CC እና ከዚያ በላይ
- የሲሊንደር ብዛት፦ ....3 ወይም 4 ሲሊንደር
- የነዳጅ አይነት፦.........Petrol
- ከፍተኛ ፍጥነት፦...........140 - 80 KM/H
- የመቀመጫ ብዛት፦5 መቀመጫ
- የበር ብዛት፦.............4 በር
ተጫራቾች ማቅረብ የሚገባቸው ሰነዶች፦
- የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ።
- የዘመኑ ግብር ለመክፈሉ ማረጋገጫ ከተገቢው መ/ቤት።
- በንግድ ድርጅት የተመዘገበ የቲን ቁጥር ያለው እና ቫት ተመዝጋቢ መሆኑን ማረጋገጫ፡
- ብቸኛ አስመጪ ከሆነ የማረጋገጫ ሰነድ ማቅረብ፡፡
- ተሽከርካሪውን ማቅረብ የሚችሉበትን የጊዜ ገደብ መግለጽ።
የጨረታ መክፈቻ
ጨረታው ጥቅምት 13/02/2019 ዓ.ም ከሰዓት 8:00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በYWCA Ethiopia ቢሮ ይከፈታል፡፡
አድራሻ፦
የወጣት ሴቶች ክርስቲያናዊ ማህበር በኢትዮጵያ (WCA Ethiopia)
4 ኪሎ፣ እክላስ ሕንፃ፣ አብረሆት ላይብረሪ አጠገብ፣ 4ኛ ፎቅ
ስልክ፦ +251 111704742/0968570579
Tender details
- Deadline: 2026-10-23
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ
- Bid opening: 2026-10-23 14:00
- Bid opening (note): ጥቅምት 13/02/2019 ዓ.ም ከሰዓት 8:00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: ወጣት ሴቶች ክርስቲያናዊ ማህበር በኢትዮጲያ (ወ.ሴ.ክ.ማ)
- Published on: Reporter (Oct 18, 2026)
- Posted at: 2026-10-20T08:17:02.000Z
- Source: Qelal Tenders