Shares and Others Foreclosure
የአክሲዮን የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት አዳነ ግደይ እና የፍ/ባለዕዳ ወንዝ ትራንስፖርት ንግድ አክሲዮን ማህበር መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 196588 በo3/07/2017ዓ/ም እና በመ/ቁጥር/210252 በ17/10/2018ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ፍርድ ያረፈበት ለተባበሩት ቢሔራዊ ፔትሮሊየም አ/ማ የሚገኙ አክሲዮን ብዛት 419 የአንዱ አክሲዮን ዋጋ 5000( አምስት ሺህ) የጠቅላላ አክሲሆን ዋጋ 2,095,000(ሁለት ሚሊዮን ዘጠና አምስት ሺህ) የአከሲዮን ትርፍ ክፍፍልን በተመለከተ እንደየ አመቱ የሚለያይ ሲሆን በባለፉት 5 አመት ታይቶ በአማካይ ከብር 250,000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ) እስከ ብር 400,000( አራት መቶ ሺህ) ከግብር በኃላ 15/100 ተቆርጦ ወደ ማህበራቸው አካወንት የገባ ሆኖ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 2,095,000/ ሁለት ሚሊዮን ዘጠና አምስት ሺህ) ሆኖ የትራዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 14 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 5 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ከፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጫረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.PO አሰርቶ በኢትዮያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ አፈ ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112739852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ እንገልጻለን፡፡
የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-23
- Bid closing time: 11:00
- Bid opening: 2026-11-23 11:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published on: Addis Zemen (Oct 22, 2026)
- Posted at: 2026-10-22T09:24:55.000Z
- Source: Qelal Tenders