Other

የኢትዮጵያ ጂምናስቲክስ ፌዴሬሽን የጂምናስቲክስ ስፖርትን ለማሳደግ፣ የገቢ ምንጮቹን ለማስፋት እና ዘላቂ የግል ዘርፍ አጋርነቶችን ለመፍጠር የማርኬቲንግ፣ የስፖንሰርሺፕ ስትራቴጂ፣ የግብይት እቅድ፣ የድርጅት አጋሮችን ቁጥር ማሳደግ እና የገቢ ማሰባሰብ አገልግሎት ሊሰጥ የሚችል ማንኛውንም ብቁ የማርኬቲንግ/ስፖንሰርሺፕ አፈላላጊ ኤጀንሲ ወይም አገልግሎት ሰጪ እንዲወዳደር ይጋብዛል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ 001/2019

የኢትዮጵያ ጂምናስቲክስ ፌዴሬሽን የጂምናስቲክስ ስፖርትን ለማሳደግ፣ የገቢ ምንጮቹን ለማስፋት እና ዘላቂ የግል ዘርፍ አጋርነቶችን ለመፍጠር የማርኬቲንግ፣ የስፖንሰርሺፕ ስትራቴጂ፣ የግብይት እቅድ፤ የድርጅት አጋሮችን ቁጥር ማሳደግ እና የገቢ ማሰባሰብ አገልግሎት ሊሰጥ የሚችል ማንኛውንም ብቁ የማርኬቲንግ/ስፖንሰርሺፕ አፈላላጊ ኤጀንሲ ወይም አገልግሎት ሰጪ እንዲወዳደር ይጋብዛል።

 የፌዴሬሽኑን የአሁኑን የግብይት ሁኔታ፣ ውድድሮችና የአጋርነት እድሎች መገምገም፣ የስፖንሰርሺፕ ስትራቴጂ፣ የዋጋ ደረጃዎች፣ የስፖንሰር ጥቅል እና የዓመት የግብይት እቅድ ማዘጋጀት፣ የሚመለከታቸውን ድርጅቶች መለየት፣ ድርድርን መደገፍ እና የስፖንሰር ግንኙነትን ማስተዳደር፣ በየሩብ ዓመቱ የሥራ እንቅስቃሴ፣ የቀረቡ ሀሳቦች፣ ገቢ የተደረገ ገንዘብ እና የተፈጸሙ ግዴታዎች ሪፖርት ማቅረብ።

በዚሁ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች

  • በሕጋዊ ሁኔታ የተመዘገበ ድርጅት መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  • ተገቢ የንግድ ፈቃድና የግብር ምዝገባ ማቅረብ የሚችል፣
  • ለፌዴሬሽኑ የሚያስገባውን ገቢ ጠቅሶ ማስገባት የሚችል፣ እያንዳንዱ ተጫራች ብር 50,000 / ሃምሳ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበርያ ሲፒኦ በፌዴሬሽኑ ስም ማቅረብ ይኖርበታል።
  • የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ካሸነፈ ብር 200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በፌዴሬሽኑ አካውንት ማስያዣ ቅድሚያ ገቢ ማድረግ አለበት።
  • የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 20,000.00 /ሃያ ሺ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ስድስት ኪሎ በሚገኘው ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር 4ኛ ፎቅ በጽ/ቤት በመቅረብ መግዛት ይቻላል።
  • ፌዴሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ማስያዝ እና የሚጠየቀውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣ ጨረታውን ካሸነፈ 200,000 ብር ማስያዝ የሚችል ማንኛውም ተጫራች መጫረት ይችላል።
    ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትንና ተያያዥ ሰነዶችን እና የገዙትን ሰነድ ኮፒ በሙሉ አያይዘው እንዲያቀርቡ ይጠየቃሉ።
  • የጨረታው መወዳደርያ ቀነ ገደብ፣ ጨረታው ከወጣ በኋላ ባሉት 10 የስራ ቀናት ውስጥ ይሆናል።

 ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡ 0911 46 80 91 / 0973-19-99-91 ወይም
0910-36-86-80 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ
የኢትዮጵያ ጂምናስቲክስ ፌዴሬሽን

 


Tender details

  • Deadline: 2026-11-04
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ጨረታው ከወጣ በኋላ ባሉት 10 የስራ ቀናት ውስጥ
  • Bid opening: 2026-11-04 17:00
  • Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለጸም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: የኢትዮጵያ ጂምናስቲክስ ፌዴሬሽን
  • Bid bond: 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 20,000.00 /ሃያ ሺ ብር/
  • Published on: Addis Zemen (Oct 24, 2026)
  • Posted at: 2026-10-24T08:29:08.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders