Catering and Cafeteria Services

ተስፋ ድርጅት ቁርስና ምሳ ምግብ የሚያቀርቡ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

Description

በድጋሜ የወጣ የምግብ አቅርቦት የጨረታ ማስታወቂያ

ተስፋ ድርጅት አገር በቀል መንግስታዊ ያልሆነ ግብረ ሠናይ ድርጅት ሲሆን በአገራችን በተለያዩ ክልሎች ማለትም በጋምቤላ፣ በአሶሳ፣ በኦሮሚያ፣ በአማራና ደቡብ ክልል እንዲሁም በአዲስ አበባ ባሉን ቅርንጫፎች በትምህርት፣ በሙያ ስልጠና እና በእለት እርዳታ ዙሪያ የሰብአዊ አገልግሎት ሥራ እየሠራ ይገኛል። ድርጅቱ ለሚረዳቸው ተማሪዎቹ፤

1. በኦሮሚያ ክልል አርሲ ነገሌ ወረዳ ሮጌ ቀበሌ በሚገኘው ት/ቤት ለሚማሩ 600 ለሚጠጉ ተማሪዎች

2. በሲዳማ ክልል በውጅግራ ወረዳ ሲንታሮ ቀበሌ ት/ቤት ለሚማሩ 615 ለሚጠጉ ተማሪዎች ቁርስና ምሳ ምግብ የሚያቀርቡ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እንዲሁም ቲን ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል ተወዳዳሪ የመወዳደሪያ ቅጽ/ሰነድ ከተስፋ ድርጅት ዋናው መ/ቤት በመውሰድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ብር 200 በመግዛት እስከ ጥቅምት 20 ቀን 2019 ፣ ከቀኑ 6.00 ሰአት ድረስ በማህተም በተረጋገጠ እና በታሸገ ፖስታ ማስገባት እንደምትችሉ እናስታውቃለን።

በህጋዊ ማህተም ያልተሸገ ፖስታ ከውድድሩ ውድቅ ይሆናል።

ጨረታው ጥቅምት 20 ቀን 2019 ከቀኑ 8:00 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።

ማሳሰቢያ፡-ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። በተጨማሪም አሸናፊ ተጫራጮች ለአንድ የትምህርት አመት 2019 ዓ.ም. ባቀረቡት ዋጋ ምግቡን የማቅረብ ሀላፊነት አለባቸው።

ከአማካይ ምግብ ዋጋ በጣም ዝቅተኛ ወይም በጣም ከፍተኛ ዋጋ ማቅረብ ከጨረታ ሊያሰርዙ ይችላሉ።

ለበለጠ መረጃ፡ ኢአ ዋናው መስሪያ ቤ/ት አየር ጤና፣ ሳሚ ካፌ ፊት ለፊት

ስልክ ቁጥር 011 348 2537 የመሳጥን ቁጥር 30153 አዲስ አበባ ወይም

ድርጅቱ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-30
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid opening: 2026-10-30 14:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Hope Enterprise
  • Buyer's registered address: አየር ጤና ሳሚ ካፌ ፊት ለፊት
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Reporter (Oct 25, 2026)
  • Posted at: 2026-10-26T12:48:52.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders