Distribution of Different products

ህሊና ገንቢ ምግቦች ኃ/የተ/የግል ማህበር ለምርትን ማከፋፍል ይፈልጋል

Description

ለምርት አከፋፋዮች የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን ህሊና ገንቢ ምግቦች ኃ/የተ/የግል ማህበር ላለፉት 28 ዓመታት በከፍተኛ ጥራት የነፍስ አድር ምርት ማለትም ፕላምፒነት እያመረተ ለእርዳታ ድርጅቶች ሲያቀርብ ቆይቷል እያቀረበም ይገኛል። አሁን ደግሞ ለሰፊው ገበያ የሚውል በከፍተኛ ጥራትና ደህንነት የሚመረት ማለዳ የሚባል የለውዝ ቅቤ ይዞ መጥቷል። ይህን ምርት የኢትዮጵያ ደረጃ መስፈርትን የሚያሟላ እና በከፍተኛ ጥንቃቄ የተመረተ ጣፋጭ ለጤና ተስማሚ የለውዝ ቅቤ ነው። ይህንን ምርት በአዲስ አበባ፣ በሸገር ከተሞችና በክፍለ ሃገር ማከፋፈል የምትፈልጉ ብቁ አከፋፋዮች ከዚህ በመቀጠል ያሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ማለትም፡-

  • ህጋዊ የታደሰ የምግብ አከፋፋይ ፍቃድ ያለው፣
  •  ምግብና መጠጥ ማከፋፈል ላይ በቂ ልምድ ያለውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
  • በቂና ደህንነቱን የጠበቀ መጋዘን ያለው፣
  • በቂ የሽያጭ ሠራተኛ እና ማከፋፈያ ትራንስፖር ያለውና
  • ጥራቱንና ደህንነቱን በጠበቀ መልኩ ማከፋፈል የሚችል

በድርጅታችን በለገጣፎ በመገኘት የድርጅታችሁን ዝርዝር መረጃ (Company Profile) እና ልምድ ማረጋገጫ ሰነድ እንዲሁም የታደሰ የምግብ አከፋፋይነት ፈቃድ እና Tin Number ኮፒ አድርጋችሁ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው 15 ቀን ውስጥ በአካል እንድታስገቡ ወይንም፡-

በEmail [email protected]  ወይንም [email protected]  እንድትልኩ ስንል በትህትና እንጠይቃለን።

ለበለጠ መረጃ በ09 44 03 65 94 ወይም 09 75 48 98 79 ይደውሉ።

 


Tender details

  • Deadline: 2026-11-09
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው 15 ቀን ውስጥ
  • Bid opening: 2026-11-09 17:00
  • Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለጸም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Hilina Enriched Food Processing Center P.L.C.
  • Published on: Reporter (Oct 25, 2026)
  • Posted at: 2026-10-26T14:09:49.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders