Service
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰ/ሸዋ ዞን የአጣዬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2019 በጀት አመት የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰ/ሸዋ ዞን የአጣዬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2019 በጀት አመት ለአንድ አመት የሚቆይ የአውት ሶርስ ስራ ማለትም ፡- የአትከልተኛ እና የጉልበት ስራ አገልግሎት
- የሰራተኞች የመኪና ሰርቪስ ፣ የጥበቃ እና ደህንነት ስራ እና ዓመታዊ ግዥዎች ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያ : ሎት 2 ቋሚ ዕቃ ፣ ሎት 3 የደንብ ልብስ ፣ ሎት 4 የኤሌትሪክ ዕቃ ፤ ሎት 5 የተለያዩ የህትመት ስራ፣ ሎት 6 የመኪና መለዋወጫ ዕቃ፣ ሎት 7 የቧንቧ ዕቃ፣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ የዘመኑን ግብር የከፈሉ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነበር ያላቸው ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
2 ህጋዊ የንግድ ፈቃድ የዘመኑን ግብር የከፈለ የግብር ከፋያ መለያ ቁጥር ያለው ጨረታው ለማሸነፍ የሠጠው አመታዊ ዋጋ ከ500,000.00 / አምስት መቶ ሺህ ብር / እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ አለበት።
3. ተጫራቾች በጨረታ በመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ኦርጅናሉንና ኮፒ በጥንቃቄ ሞልተው በየሎቱ ማስገባት እና ማቅረብ አለባቸው።
4. ዝርዝር መግለጫ እስቴስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ :: የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 / ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመያዝ በአጣዬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ ፋይናስ ገንዘብ ቤት መግዛት ይችላሉ።
5. ተጫራቾች ጨረታ ከመከፈቱ በፊት የተወዳደሩበትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 1% እና ካሸነፈ በኋላ ያሸነፈበትን ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም ሲፒኦ በጥሬ ገንዘብ ሆስፒታሉ ገንዘብ ቤት ድረስ ቀርበው ማስያዝ አለባቸው።
6 ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በቢሮ ግዥ ፋይናስ ቁጥር 44 የስራ ሂደት በዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰአት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ሰአት ላይ ጨረታ ማስገባት ትችላላችሁ። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወዲያው ይታሸጋል ወዲያው 4፡10 ላይ ይከፈታል፣
7 ተማሪ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥ ፋን አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት በስልክ ቁጥር በሞባይል 0913675704 /093034113 /0913005480/0913023571 ቁጥር በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
8, ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ፀንቶ ለ 05 / አምስት ) ቀን ይቆያል።
9 የመክፈቻው ዕለት በአል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
10.ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ማስታወቂያ ላይ ያልተገለፁትን ሁኔታዎች ቢኖሩ በግዥ መመሪያው ተግባር መሆን አለባቸው።
11. ለወሰዱት የተጫራቾች መመሪያ ለእያንዳንዱ ገፅ ላይ የድርጅታችሁን ማህተም ማድረግ እና አብረው ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
12 ግብር የከፈሉበት ክሪላንስ ከገቢዎች ፅ/ቤት አብረው ማስያዝ አለባቸው።
13. ውድድሩ የምናወዳድረው በጥቅል ነው።
14. ስርዝ ድልዝ ካለው ውድድሩ ሙሉ ለሙሉ ውድቅ ይደረጋል።
15. ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰ/ሸዋ ዞን
የአጣዬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
Tender details
- Deadline: 2026-11-11
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰአት
- Bid opening: 2026-11-11 10:10
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡10 ሰአት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Ataye Primary Hospital
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 27, 2026)
- Posted at: 2026-10-27T09:32:13.000Z
- Source: Qelal Tenders