Products and Services

ባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ አክስዮን ማህበር ለፋብሪካ ግብዓት የሚውል 6,700 ኩ/ል የተዳመጠ ጥጥ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር፣ ባ/ጨ/ጨ/ግ/አቅ/001/2019

ባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ አክስዮን ማህበር ለፋብሪካ ግብዓት የሚውል 6,700 ኩ/ል የተዳመጠ ጥጥ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል፡፡

1. ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች-

  • ሕጋዊ ፈቃድ፡- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው።
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT)፡- በቫት (VAT) ተመዝጋቢ ሆነው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  • የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም የባንክ ዋስትና መጠን የተጫረተበትን ጠቅላላ ዋጋ 1% ማስያዝ የሚችሉ።

2. የጨረታ ሰነድ አቀራረብ እና አሰጣጥ፡-

  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200 ብር (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ሰነዱን ባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ አ/ማ ወይም አ/አበባ ማስተባበርያ ጽ/ቤት ማግኘት ይችላሉ፡፡
  • የጨረታ ሃሳብ የያዘው ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ዋናው እና ኮፒው ጫረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ቀናት ውስጥ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

3. የጨረታ መክፈቻ ሁኔታ፡-

  • የጨረታው መክፈቻ ጊዜ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ጨረታው በ21ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ባህርዳር ጨርቃ ጨርቅ አ.ማ ግዥና ንብረት አስተዳደር መመሪያ ይከፈታል። የጨረታው መክፈቻ ዕለት የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡

4. መብት፡-

  • ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ

ስልክ ቁጥር፡

ባህር ዳር 058 220 0080 / 0900 911 834

አዲስ አበባ 0115 531 381 / 0115 539 742

ቦታ አድራሻ፣ ባህር ዳር ከተማ ግሽ አባይ ክ/ከተማ ቀበሌ 10

ባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-11-16
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ቆይቶ በ21 ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-16 14:30
  • Bid opening (note): ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ቆይቶ በ21 ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Bahir Dar Textile S.C.
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 26, 2026)
  • Posted at: 2026-10-27T10:48:43.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders