Catering and Cafeteria Services

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል በ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ ግዥዎችን ለሁለተኛ ዙር በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር አ/አ/ከ/አ/ለነ/ሴ/ተ/ክ/ማ/ማ (01/001-03/2019)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል በ2019 በጀት ዓመት በ3 ሎት የተከፈሉ ግዥዎችን ለሁለተኛ ዙር በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት ቁጥር

የሚገዛው እቃ አገልግሎት

የጨረታ ማስከበሪያ መጠን

ሎት 1

የሰልጣኞች ምግብ ለማቅረብ በምናቀርበው የምግብና መስተንግዶ ዝርዝር በቀን ሦስት ጊዜ ማቅረብ

100,000.00 cpo

ሎት 2

ለሠራተኞች ካፊቴሪያ ለማቅረብ በምናቀርበው የምግብና መስተንግዶ ዝርዝር መሰረት ማቅረብ

100,000.00 cpo

ሎት 3

የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጀር

300,000.00 cpo

ስለዚህ ከዚህ ቤታች የተዘረዘሩትን የግዥና ፋይናንስ መመሪያዎችን የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡

1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2. በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መኖራቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡

3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin) ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ።

4. የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

5. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተጫራቾች ከተደራጁበት ክፍለ ከተማ ወይም ወረዳ በመስሪያ ቤቱ የፅህፈት ቤት ኃላፊ ስም የተፈረመ - ወቅታዊ የድጋፍ ደብዳቤ እና አምራች መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) ብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአካውንት ቁጥር 1000640967181 በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት እስከ 11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ከማዕከሉ ከፋይናንስ ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ በስፔስፊክሽኑ መሰረት ብቻ በማድረግ ቫትን ጨምረው ሞልተው በታሸገው ኤንቨሎፕ ላይ ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒ ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ ብለው በአራት ፖስታ በመለየት የግዥ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከላይ በሰንጠረዥ በተገለፀው መሰረት ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

8. ተጫራቾች ሌሎች መረጃዎችን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤

10. ጨረታው በሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።

11. ተጫራቾች ናሙና ለተጠየቀባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው።

12, የጨረታ ማስከበሪያ በCPO ነው፡፡

ማሳሰቢያ፤ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ውክልና ያላቸው አካላት በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡

አድራሻ - አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ጀርባ 500 ሜትር ገባ ብሎ ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶ እና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል 1ኛ ፎቅ የግዥ ንብረትና ህንፃ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ

ስልክ ቁጥር:- 0111 437 8666

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶ እና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል


Tender details

  • Deadline: 2026-11-06
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-06 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa City Administration Lnegewa Setoch Rehabilitation Center
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published on: Addis Zemen (Oct 26, 2026)
  • Posted at: 2026-10-27T10:53:06.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders