Products and Services
አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ ግዥ ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የአፈር ማከሚያ የግብርና ኖራ በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ ግዥ ፋይናንስ
እና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
የብድር ቁጥር / DDA Credit #:TF-B8450
የአፈር ማከሚያ የግብርና ኖራ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ ግዥ ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የዘላቂ መሬት አያያዝ ፕሮግራም (RLLP-ll፤KEW-CA እና KFW-CSA) በአለም ባንክ እና ጀርመን ባንክ የበጀት ድጋፍ በግዥ መለያ ቁጥር- ET-AMHARA BOA-535180-GO-RFB በፕሮጅክቱ ለታቀፉ ወረዳወች አገልግሎት የሚውል 50,978 (ሀምሳ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባ ስምንት) ኩንታል የአፈር ማከሚያ የግብርና ኖራ ግዥ ከነትራንስፖርቱ በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራች ድርጅቶች ሠሠዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ እና የግብር ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ።
- የግብረ ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤
- የግዥው መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማደረግ ከኦርጅናሉ ጋር በማገናዘብ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚገዛው የአፈር ማከሚያ የግብርና ኖራ ግዥ ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ እና መቅረብ ያለባቸው አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
- የጨረታ ሂደቱ በአለም ባንክ የግዥ ስርአት መሰረት የሚካሄድ ሲሆን በእቃ እና ግንባታ ግዥ ጋይድ ላይን (World Banks procurement Regulations for Borrowers governing the procurement of Goods, Works, Non-consulting services, and Consulting Services for Bank lPF projects revised February 2025) መሰረት ብቁ የሆነ ማንኛውም አገር በውድድሩ መሳተፍ ይችላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00/አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 20 ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዕቃ ብር 2,000,000.00 /ሁለት ሚሊዮን ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ከዋጋ ማቅረቢያዉ ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው የሚከተለው የአንድ ፖስታ ስርአት በመሆኑ ማንኛውም ተጫራች የቴክኒካል ፣ የፋይናንሻል ሰነዱን እና የጨረታ ማስከበሪያውን በአንድ ላይ በማድረግ በሁለት ፖስታዎች ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ግብርና ቢሮ ግቢ ቢሮ ቁጥር 027 ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30(ሰላሳ) ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
በተጨማሪም ለተጠየቀው ኖራ ማቅረቢያ የሚጠቀሙበትን መቋጠሪያ ላምኔትድ የሆነ ቀረጢት አንድ ናሙና ለብቻው በአንድ ፖስታ አሽገው ጨረታው ከመከፈቱ በፈት ማቅረብ አለባቸው።
9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግብርና ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ 31ኛ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይንም የበዓል ቀን ከሆነ በግልጽ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠው ቀን እና ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
10. በጨረታው ለመሳተፈ የሚፈለጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ዘወትር በስራ ሰአት ቢሮ ቁጥር 27 ድረስ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058-22066431/0918000340/ በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
11. በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህጎችና ደንቦች በግዥ መመሪያው እና በጨረታ ሰነዱ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል።
ቢሮ ቁጥር 017: በስልክ ቁጥር 058-22066431፤በፋክስ ቁጥር 0582208771
ባህር ዳር፤ኢትዮጵያ
አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ
ግዥ ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
Tender details
- Deadline: 2026-11-26
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30(ሰላሳ) ተከታታይ ቀናት
- Bid opening: 2026-11-27 17:00
- Bid opening (note): ጨረታው 31ኛ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይንም የበዓል ቀን ከሆነ በግልጽ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠው ቀን እና ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል
- Region: Amhara
- Publishing entity: Amhara National Regional State Agriculture Bureau
- Bid bond: 2,000,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 28, 2026)
- Posted at: 2026-10-28T08:47:32.000Z
- Source: Qelal Tenders