Architectural and Construction Design

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በሥሩ በሚገኙ በ 3 (ሦስት) ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች (አሰላ፣ አርዳይታ እና ኮፈሌ ሳይቶች) የምድር ሚዛን ከነገጠማው እንዲሁም የሲቪል ሥራዎችን (Design & Construct) ጨምሮ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ኢ.ግ.ሥ.ኮ/

ብግጨ/4/2019

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ2019 በጀት ዓመት በሥሩ በሚገኙ በ 3 (ሦስት) ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ማለትም አሰላ፤ አርዳይታ እና ኮፈሌ ሳይቶች የምድር ሚዛን ከነገጠማው እንዲሁም የሲቪል ሥራዎችን (Design & Construct) ጨምሮ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው ዝርዝር መስፈርት መሰረት በማቅረብ ሁሉንም (Supply installation, testing, Commissioning, training & Civil works (Design & Construct) መስራት የሚችሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ በዘርፉ ንግድ ፈቃድ ያላችሁና የዘመኑን ግብር ለመክፈላችሁ ማስረጃ፣ የቫት ተመዝጋቢ ቲን፤ እና በEGP የአቅራቢዎች ሊስት የተመዘገበ ስለመሆኑ ማስረጃ መቅረብ ይኖርበታል ፡፡ እንዲሁም ከገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ቃሊቲ ጉምሩክ ከባቡር መነሻ ፊት ለፊት በሚገኘው አዋሽ ባንክ በኩል ወደ ውስጥ በሚያስገባው መንገድ ገባ ብሎ በሚገኘው የቀድሞ የግብርና ግብዓት አቅርቦት ዘርፍ ህንፃ 3ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 306 ግዥ ክፍል ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ ብር 400,000.00 (አራት መቶ ሺህ ብር ብቻ) በሲፒኦ ወይም በባንከ ጋራንቲ (Unconditional) ማሲያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጨረታ ዋጋ ለ60 (ስልሳ) ቀናት የጸና መሆን ይኖርበታል፡፡ ጨረታው ህዳር 1 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የስብሰባ አዳራሽ ቴክኒካል የጨረታ ሰነድ የመክፈቻ ስነ-ሥርዓት ይከናወናል። ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- ስልክ +251911984467 ወይም +251910567578

ፋክስ 0114-421312

አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-11-10
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-11-10 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Agricultural Business Corporation
  • Buyer's registered address: ከሳሪስ ፋፋ የምግብ አክሲዮን ማህበር ወደ ውስጥ ገባ ብሎ
  • Bid bond: 400,000.00 ብር
  • Bid document price: 400.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 30, 2026)
  • Posted at: 2026-10-30T08:06:21.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders