Other

የኢትዮጵያ ጂምናስቲክስ ፌዴሬሽን የማርኬቲንግ፣ የስፖንሰርሺፕ እና ኮሚዩኒኬሽን ስትራቴጂ፣ የግብይት እቅድ ማውጣት፣ እና የገቢ ማሰባሰብ አገልግሎት የሚሰጥ አማካሪ ኤጀንሲ በጨረታ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ የጨረታ
ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር- 002/2019

የኢትዮጵያ ጂምናስቲክስ ፌዴሬሽን የጂምናስቲክስ ስፖርትን ለማሳደግ፣ የገቢ ምንጮቹን ለማስፋት እና ዘላቂ የግል ዘርፍ አጋርነቶችን ለመፍጠር የማርኬቲንግ፣ የስፖንሰርሺፕ እና ኮሚዩኒኬሽን ስትራቴጂ፣ የግብይት እቅድ ማውጣት፣ እና የገቢ ማሰባሰብ አገልግሎት ሊሰጥ የሚችል ማንኛውንም ብቁ የማርኬቲንግ/ ስፖንሰርሺፕ አፈላላጊ እና አማካሪ ኤጀንሲ ወይም አገልግሎት ሰጪ እንዲወዳደር ይጋብዛል።

የስራው ዝርዝር፦ የፌዴሬሸኑን የአሁኑን የግብይት ሁኔታ፣ ውድድሮችና የአጋርነት እድሎች መገምገም፣ የስፖንሰርሺፕ እና የማርኬቲንግ ስትራቴጂ ማውጣት፣ የዋጋ ደረጃዎች፣ የስፖንሰር ጥቅል እና የዓመት የግብይት እቅድ ማዘጋጀት፣ የማርኬቲንግ እና ኮሚዩኒኬሽን እቅድ አውጥቶ ማማከር እና መተግበር፣ የሚመለከታቸውን ድርጅቶች መለየት፣ ድርድርን መደገፍ እና የስፖንሰር ግንኙነትን ማስተዳደር፣ በየሩብ ዓመቱ የሥራ እንቅስቃሴ፣ የቀረቡ ሀሳቦች፣ ገቢ የተደረገ ገንዘብ እና የተፈጸሙ ግዴታዎች ሪፖርት ማቅረብን የሚያካትት ይሆናል።

በዚሁ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች

  • በሕጋዊ ሁኔታ የተመዘገበ ድርጅት መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  • ተገቢ የንግድ ፈቃድና የግብር ምዝገባ ማቅረብ የሚችል፣
  • ለፌዴሬሽኑ የሚያስገባውን ገቢ ጠቅሶ ማስገባት የሚችል፣ እያንዳንዱ ተጫራች ብር 20,000/ሃያ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበርያ ሲፒኦ በፌዴሬሽኑ ስም ማቅረብ ይኖርበታል።
  • የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ካሸነፈ በኋላ ኮንትራት እንደተፈራረመ፣ ብር 200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በፌዴሬሽኑ አካውንት ማስያዣ ቅድሚያ ገቢ ማድረግ አለበት።
  • የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 5000.00 /አምስት ሺህ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰአት ስድስት ኪሎ በሚገኘው ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር 4ኛ ፎቅ በጽ/ቤት በመቅረብ መግዛት ይቻላል።
  • ፌዴሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትንና ተያያዥ ሰነዶችን በሙሉ አያይዘው እንዲያቀርቡ ይጠየቃሉ፡
  • የጨረታው መወዳደርያ ቀነ ገደብ፣ ጨረታው ከወጣ በኋላ ባሉት 5 /አምስት/ ቀናት ውስጥ ይሆናል።

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0911-46-80-91/ 0973-19-99-91 ወይም 0910-36-86-80 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ጂምናስቲክስ
ፌዴሬሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-11-09
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ጨረታው ከወጣ በኋላ ባሉት 5 /አምስት/ ቀናት ውስጥ
  • Bid opening: 2026-11-09 17:00
  • Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰአት አልተገለፀም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: የኢትዮጵያ ጂምናስቲክስ ፌዴሬሽን
  • Bid bond: 20,000 (ሀያ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 5000.00 /አምስት ሺህ ብር/
  • Published on: Addis Zemen (Nov 04, 2026)
  • Posted at: 2026-11-04T08:11:12.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders