Land Lease & Real Estate

የሐረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግሥት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ባለሥልጣን ያወጣውን የሊዝ ጨረታ ማስተካከያ አድርጎበታል

Description

የ10ኛ ዙር የጀጎል ሞዴል መንደር የሊዝ 

ጨረታ ጊዜን ማራዘም ማስታወቂያ

የሐረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግሥት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ባለሥልጣን በሐረር ከተማ ጀጎል አባድር ፕላዛ አካባቢ (የጀጎል ሞዴል መንደር) ለመኖሪያ (63 ፓርስሎች) ለንግድ መደብሮች (31 ፓርስሎች) እና ለካፌ ንግድ (1 ፓርሰል) በጠቅላላው 95 ፓርስሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስተላለፍ ጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓ.ም. ጨረታ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሳል። ሆኖም ተወዳዳሪዎች አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉና ሰፊ የምዝገባ እድል ለመስጠት ሲባል የጨረታ ሰነድ መግዣ መመለሻና መከፈቻ ጊዜ ለተጨማሪ 10 የሥራ ቀናት ማራዘም አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል። 

በዚሁ መሠረት፦

የሰነድ ሽያጭና ማስገቢያ የመጨረሻ ቀን፦ እስከ ህዳር 10 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ድረስ ተራዝሟል። የጨረታ ሳጥን የሚዘጋበት ጊዜ፦ ህዳር 10 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ ይሆናል።

የጨረታ ሳጥን የሚከፈትበት ጊዜ፦ ህዳር 10 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ 4ኛ ፎቅ አዳራሽ ይከናወናል። የሰነድ መግዣ አማራጮች፦ በኦንላይን ፖርታል https://sltms.hararsmartlandsystem.gov.et  በመግባት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000017606364 ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ በማያያዝ ወይም በአካል በመቅረብ በመሶብ 1 ማዕከል እንዲሁም በዋናው መሥሪያ ቤታችን ምድር ቤት ቢሮ ቁጥር 49 መግዛት ይቻላል። ከዚህ ቀደም በጨረታ ማስታወቂያው ላይ የወጡት የCPO መጠን (5%) አነስተኛ የቅድመ ክፍያ መጠን (20%) የሰነድ ዋጋ (1,500.00 ብር) እና የማወዳደሪያ መስፈርቶች (80/20)እንደተጠበቁ ናቸው።

ለተጨማሪ መረጃ በባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ይፋዊ ድረ-ገፅ https://hudco.gov.et በመግባት ወይምበአካል ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል።

በሐ/ሕ/ክ/መ/ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ባለሥልጣን

ከዚህ በፊት የወጣውን ጨረታ ለመመልከት እባክዎን ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ 
https://tenders.qelal.et/tender-6ada03490a538ab8cc000001/ 


Tender details

  • Deadline: 2026-11-19
  • Bid closing time: 09:00
  • Bid opening: 2026-11-19 10:00
  • Region: Hareri
  • Publishing entity: Harari City Government City Development Construction Office
  • Bid bond: የጠቅላላው የቦታ ስፋት በመነሻ ዋጋው ተባዝቶ ከሚገኘው ውጤት 5% (አምስት ፐርሰንት)
  • Bid document price: 1500.00 /አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር/
  • Published on: Addis Zemen (Nov 05, 2026)
  • Posted at: 2026-11-05T07:35:59.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders