Other

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ሁለት (2) የተለያዩ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን ማሰራት ይፈልጋል

Description

ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ 003/2019

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የኮሚሽኑን ራዕይ እና ተልዕኮ ማሳካት የሚያስችሉ 

  • ሎት 1- ሁለት (2) የተለያዩ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን፤-

በአዲስ አበባ ከተማ ቀዳሚ የኢንቨስትመንት አማራጮች፤ እድሎችና የወደፊት አቅጣጫዎች (Investment priorities, opportunities, and future Directions in Addis Ababa) 

በአዲስ አበባ ከተማ የባለድርሻ አካላት ትስስር እና የኢንቨስትመንት እድገት (The integration of stakeholders and the growth of investment in Addis Ababa City) (2019 በጀት ዓመት በውጭ አቅም (Consultants) በዘርፉ የተሰማሩና ብቁ የሆነ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስጠናት አስፈልጓል።

ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው ህጋዊ እና እውቅና ማረጋገጫ መስፈርቶች፦

1.ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማራችሁ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ክሊራንስ ሰርተፍኬት፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ፤ የታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት፤ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤

2.በግዢና ንብረት ባለሥልጣን የዕቃዎችና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

ለጥናቱ ሥራ የተቀመጡ ልዩ የብቃት መመዘኛዎች፤

የሥራ ልምድ፤- ጥናቱ የሚያጠኑ አካላት በማስተርስ ዲግሪ ቢያንስ 6 ዓመት በፒኤችዲ 5 ዓመት አጠቃላይ በጥናት ስራና ተዛማች ስራዎች ላይ ልምድ ያላቸው፤ 3 ተመሳሳይ የጥናት ፕሮጀክቶችን በተሳካ ሁኔታ ያጠናቀቁ ለተሰሩ ስራዎች መረጃ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ።

የትምህርት (ዝግጅት እና ዓይነት) ለጥናት ሥራው የተሰማሩት ባለሙያዎች ሥራውን ለመሥራት የሚያስችል ተገቢና ተዛማጅ የሆነ ከፍተኛ የትምህርት ዝግጅት (እውቅና ካለው የትምህርት ተቋም በማኔጅመንት፤ በኢኮኖሚክስ፣ በልማት ጥናት፤ ውይም በተመሳሳይ ተያያዥ መስኮች ቢያንስ የማስተርስ ዲግሪ ውይም ፒኤችዲ ያለው/ላት) ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ።

ለጥናቱ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን መረጃዎችን ታማኝ ከሆነ የመንግሥት ተቋማት እና አስተማማኝ ምንጮች ብቻ ተጠቅሞ የመሥራት ግዴታ አለበት።

እያንዳንዱን የጥናት ሥራ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች (በትርጉም) ማዘጋጀት የሚችል፡፡ 

እያንዳንዱን የጥናት የሥራ ውል ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ በ4 (አራት) ወራት ጊዜ ውስጥ አጠናቆ በሃርድ ኮፒ (Hard Copy) እና በሶፍት ኮፒ (Soft Copy) ማስረከብ የሚችል።

የጨረታ አቀራረብ እና መመሪያዎች፦

3. ተጫራቾች የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ) የኢትዮጵያ ብር በመከፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ሜክሲኮ ሰንጋተራ ዮቤክ ኮሜርሻል ሴንተር 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 802 በግዥ፤ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።

4. ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ለሎት 1፤- ለሁለቱም 30,000 (ሰላሳ ሺህ) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) የባንክ ዋስትና ከቴክኒክ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አሥር) ተከታታይ የስራ ቀናት (ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ከቀኑ 11፡00) ከፍት ሆኖ ይቆያል።

6. የቴክኒክ ብቃት (የመጀመሪያዎቹ 5 መስፈርቶችና የንግድ ፈቃድ ማስርጃዎች ) እና የፋይናንስ ዋጋ አቅርቦት በተለያዩ ኤንቨሎፕ ኦርጅናል እና ኮፒ መቅረብ ይኖርበታል፡፡

7. ጨረታው በተዘጋበት በ11ኛው ቀን ጠዋት 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ሜክሲኮ ሰንጋተራ ዮቤክ ኮሜርሻል ሴንተር 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 802 በግዢ፣ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ይከፈታል፡፡ (የመዝጊያ እና መክፈቻው ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚዘጋ እና የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን)፡፡ 

8. አሸናፊው ተጫራች ውል ከመፈረሙ በፊት የውል ማስከበሪያ ማቅረብ ይኖርበታል።

9. አሸናፊ ተጫራቾች አሸናፊነቱ በተገለፀበት ከ05 /አምስት/ ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ በግንባር ቆርቦ አሸናፊ የሆነበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 % የውል ማስከበሪያ በማስያዝ በ 07/ሰባት ቀናት ውስጥ ውል መያዝ የሚችል መሆን አለበት፤

10. ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ተካፋይ ሆኖ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የተሰጠውን ዋጋ ለማሻሻል፣ ለመለወጥ ወይም ትቼዋለሁ ማለት አይችልም፤

12. ማንኛውም ተጫራች ማጭበርበር ወይንም ሙስናን በተመለከተ በኢትዮጵያ ህጎች የተደነገገውን የሚያከብር መሆን ይገባዋል፤

13. ጨረታውን ለማዛባት ሙከራ የሚያደርግ ተጫራች ከጨረታው እንደሚሰረዝ እና ወደፊትም

ማሳሰቢያ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንስትመንት ኮሚሽን ሜክሲኮ ሰንጋተራ ዮቤክ ኮሜርሻል ሴንተር 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 802 በግዢ፤ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መረጃ ማግኘት ይቻላል::

ለተጨማሪ መረጃም በስልክ ቁጥር 0115-5778-46 ደውሎ ማናገር ይቻላል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ኮሚሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-11-19
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት (ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:30 እስከ ከቀኑ 11:00)
  • Bid opening: 2026-11-20 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በተዘጋበት በ11ኛው ቀን ጠዋት 4:30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa Administration Investment Commission
  • Buyer's registered address: ልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 09 ዮቤክ ኮሜርሽያል ሴንተር
  • Bid bond: ለሁለቱም 30,000 (ሰላሳ ሺህ) ብር
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ) ብር
  • Published on: Addis Zemen (Nov 08, 2026)
  • Posted at: 2026-11-09T11:58:45.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders