Stationery

በድሬደዋ አስተዳደር የቀበሌ 01 አስ/ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በድሬደዋ አስተዳደር የቀበሌ 01 አስ/ጽ/ቤት የተለያዩ አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎች የዕቃዎች፡የአሌከሮኒክ እቃዎች እና አላቂ የት/ት መርጃ መሣሪያዎች ለመማር ማስተማር የሚረዱ እና የተለያዩ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን ።

  1. የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ና የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል።
  2. የመንግስት ግዥ ላይ እንዲሳተፍ የሚገልጽ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡።
  3. የተጫራቾች ተጨማሪ የእሌት ታክስ VAT ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል።
  4. ተጫራቾች ጨረታ ማስረከቢያ በባንክ የተረጋገጠ (CPO) 5000 (አምሰት ሺህ ብር) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል።
  5. ተጫራቾች በእያንዳንዱ ዕቃዎች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለጽ በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በዚህ በተዘጋጀ ጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በመልዕክተ ድሬ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ድሬደዋ በሚገኘዉ ቀበሌ 01 አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 8 በመምጣት ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ከፍለዉ የጨረታ ሰነዱን መዉሰድ ይችላሉ።
  7. የጨረታ ማስታወቂያ ሰነዱ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ዉስጥ ክፍት ሆኖ ከቆየ በኋላ በ16ኛዉ ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 4፡05 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በቀበሌ 01 አስተዳደር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 ይከፈታል ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ይከፈታል።
  8. አሸናፊ ተጫራች ያሸነፋቸዉን ዕቃዎች በሙሉ በገባዉ ዉል መሠረት ቀበሌ 01 አስ/ጽ/ቤት በመምጣት ንብረት ከፍል ማስረከብ ይኖርበታል።
  9. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
  10. የሚቀርቡት እቃዎች የጥራት ደረጃውን የጠበቁ መሆን አለባቸው።

ማሳሰቢያ፡-

  • ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ ከቀረበው (Specification) ውጪ ለሌለ ተመሳሳይ ዓይነት በናሙና ታይቶ መጨመር ይቻላል።
  • ማንኛውም ተጫራች ዋጋውን በዚህ ዶክመንት ላይ ሞልቶ ማህተም አድርጎ መመለስ አለበት፡፡ ጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ሲመጡ የንግድ ፍቃድ ና የምዝገባ ሰርተፊኬት ኦርጅናል ና ፎቶ ኮፒ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • የክፍያ ደረሰኞች በየሎቱ ማዘጋጀት ይኖርበታል።
  • ጨረታው ተከፍቶ ለአሸናፊዎች ከተገለፀ በኋላ የሚያቀርቧቸውንም እቃዎች እያንዳንዱ ለቅድሚያ ሳምፕል ወይም ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
  • ለበለጠመረጃ፡- 0920 909 720/0915 121 961 የመስመርስልክ፡ 025 116 0386

በድሬዳዋ አስተዳደር የወረዳ 01 አስተዳደር


Tender details

  • Deadline: 2026-11-19
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያ ሰነዱ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ዉስጥ ክፍት ሆኖ ከቆየ በኋላ በ16ኛዉ ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-19 10:05
  • Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያ ሰነዱ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ዉስጥ ክፍት ሆኖ ከቆየ በኋላ በ16ኛዉ ቀን ጠዋት 4፡05 ሰዓት
  • Region: Dire Dawa
  • Publishing entity: በድሬዳዋ አስተዳደር የወረዳ 01 አስተዳደር
  • Bid bond: 5000 (አምስት ሺህ ብር)
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Melekite Dire (Nov 04, 2026)
  • Posted at: 2026-11-09T14:20:51.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders
Could not load content