Food Items and Drinks

አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት የታሸገ ውሃ (1/2 ሊትር) እና ቆሎ (ባለ 1 ኪሎ) እና ድፎ ዳቦ (ባለ 5 ኪሎ) በማዕቀፍ ስምምነት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ግዥ መለያ ቁጥር አአከአአድ/ብግጨቁ/025/2019

አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ በግዥ መለያ ቁጥር አአከአአድ/ብግጨቁ/025/2019

  • ሎት 1፡ የታሸገ ውሃ (1/2 ሊትር) እና
  • ሎት 2፡ ቆሎ (ባለ 1 ኪሎ) እና ድፎ ዳቦ (ባለ 5 ኪሎ) በማዕቀፍ ስምምነት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በመስኩ የተሰማሩና ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው አቅራቢዎች (ድርጅቶች) ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን፡-

  1. በዘርፉ የተሰማራ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ኮፒ (Valid Trade Licensee)፣
  2. በመንግስት ግዥ ላይ ለመሳተፍ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመግባቱ በድረ-ገፅ የተመዘገበበት ኮፒ፣
  3. የታክስ ከፋይ የምዝገባ ሰርተፍኬት፣
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት ኮፒ (VAT Certificate)፣
  5. በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ፈቃድ (Valid Tax Clearance Certificate)፣
  6. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ ለሎት 1 ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ) እና ለሎት 2 ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ) በማቅረብ በግልፅ ጨረታው ላይ መወዳደር ይችላሉ፡፡

በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ አቅራቢዎች (ድርጅቶች) ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ እስከ ምሳ ሰዓት (6፡00 ሰዓት) የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በጥሬ ገንዘብ በመክፈል በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ 22 እየሩስ ህንጻ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋናው መ/ቤት (ማዕከል) የግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 ወይም 7–01 መውሰድ ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናል እና ኮፒ በመለየት እስከ ህዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ በግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ህዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ጠዋት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 ይከፈታል፡፡

ማሳሰቢያ፡-
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር፡- 011 666 3206
አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ  አገልግሎት ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-26
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-11-26 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa City Bus Service Organization
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Nov 10, 2026)
  • Posted at: 2026-11-10T08:07:18.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders