Equipment and Accessories

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሪደርና ወንዝ ዳርቻ ልማት አስተዳደር ባለስልጣን የተለያዩ ዕቃዎችንና አገልግሎቶችን ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሠራት ይፈልጋል

Description

የግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሪዶርና ወንዝ ዳርቻ ልማት አስተዳደር ባለስልጣን የተለያዩ ዕቃዎችንና አገልግሎቶችን ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሠራት ይፈልጋል።

1. ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።

  • በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤
  • የኦላይን ሰፕላይ ሬጅስትሬሽን ሰርቲፊኬት፤
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፤
  • የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ መረጃ ማቅረብ የሚችል፤

2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜን ጨምሮ ለተከታታይ ለ10 (አስር) ቀናት ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎችና አገልግሎቶች የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከተቋማችን 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 607 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፤

3. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በሚወዳደሩበት ሎት ዓይነት የተመለከተውን የጨረታ ማስከበሪያ የገንዘብ መጠን በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ የዋስትና ደብዳቤ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

የሚገዛው ዕቃና አገልግሎት ሎት

የሚገዙ ቋሚና አላቂ ዕቃዎች እና አገልግሎቶች በሎት

ማስያዝ ያለባቸው የጨረታ ማስከበሪያ

ሎት 1

የህትመት አገልግሎት ግዥ

ብር 5,000.00

ሎት 2

ኤሌክትሮኒክስና የአይሲቲ ዕቃዎች ግዥ

ብር 10,000.00

ሎት 3

የሻተር መጋረጃ እና የወለል ምንጣፍ ግዥ

ብር 5,000.00

ሎት 4

የተሽከርካሪ ጎማ፤ ቼርኬ፤ ታፒሰሪና አከሰሰሪ ግዥ

ብር 5,000.00

ሎት 5

አላቂ የጽ/መሣሪያዎች ግዥ

ብር 3,000.00

ሎት 6

የቢሮ ቁሳቁስ ጥገና አገልግሎት ግዥ

ብር 3,000.00

ሎት 7

የተለያዩ የፅዳት ዕቃዎች ግዥ

ብር 3,000.00

ሎት 8

የጉልበት ሥራ አገልግሎት ግዥ

ብር 2,000.00

ሎት 9

ለፓርኮችና አረንጓዴ ቦታዎች የሚያስፈልጉ ግብዓቶች ግዥ አሸዋ፣ ሲሚንቶ፣ ብረታብረቶች... ወዘተ/

ብር 10,000.00

ሎት 10

የፓርክና ወንዞች የደረቅ ቆሻሻዎች የፅዳት አገልግሎት

ብር 2,000.00

ሎት 11

የደረቅና ፈሳሽ ተሸከርካሪ ኪራይ አገልግሎት ግዥ

ብር 20,000.00

ሎት 12

የፕሪንተር፤ ኮምፒዩተርና ፎቶ ኮፒ ማሽን ጥገና አገልግሎት

ብር 3,000.00

ሎት 13

የፕሮዳክሽን ሥራዎች አገልግሎት ግዥ

ብር 5,000.00

ሎት 14

የጽዳት አገልግሎት ግዥ

ብር 5,000.00

4. ተጫራቾች ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ቢሮ ቁጥር 607 ድረስ በመምጣት ፋይናንሺያል እና ቴክኒካል በሚል በሁለት ፖስታ ኦርጅናል እና ኮፒ ሰነድ በተለያየ ፖስታ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤

5. ጨረታው በአየር ላይ በዋለበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን 4ኪሎ ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ 6ኛ ፎቅ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት ይከፈታል።

6. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

7. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበት የቋሚና አላቂ ዕቃዎች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሰረት አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሪደርና ወንዝ ዳርቻ ልማት አስተዳደር ባለስልጣን በመገኘት በመረከብ በራሱ ትራንስፖርት የማድረስና ለማድረሱ መተማመኛ የማቅረብ ይኖርበታል።

8. የቅድመ ጨረታ ውይይት ህዳር 10 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 607 በመገኘት መሳተፍ ይችላሉ።

9. ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- 4 ኪሎ ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 607

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሪደርና ወንዝ ዳርቻ ልማት አስተዳደር ባለሥልጣን


Tender details

  • Deadline: 2026-11-21
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በአየር ላይ በዋለበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-21 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በአየር ላይ በዋለበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሪደርና ወንዝ ዳርቻ ልማት አስተዳደር ባለሥልጣን
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Nov 10, 2026)
  • Posted at: 2026-11-10T12:26:06.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders