Equipment and Accessories
ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ አ.ማ. ላሉት ደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች የአቅጣጫ ማመላከቻ መቆጣጠሪያ እና የነዳጅ አጠቃቀም መቆጣጠሪያ መሳሪያ (GPS Vehicle Tracking System and Fuel Level Sensor) ማሰራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር Gada/NCB/02/2019
ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ አ.ማ ላሉት ደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች የአቅጣጫ ማመላከቻ መቆጣጠሪያ እና የነዳጅ አጠቃቀም መቆጣጠሪያ መሳሪያ (GPS Vehicle Tracking System and Fuel Level Sensor) ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
1. በዘርፉ የተሰማሩ ፤የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ እንዲሁም ንግድ ምዝገባ ምስክር እና ሌሎች አስፈላጊውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
2. ማንኛውም ተወዳዳሪ ተጫራች የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሲሆን ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 12ኛ ፎቅ ከጠዋቱ 2፡30 እሰከ 11፡00 በመምጣት የማይመለስ 500 (አምስት መቶ) ብር በመክፍል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡
3. ማንኛውም ተጫራች በገዛው የጨረታ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም በማድረግ እና በመፈርም በሰም በታሸገ ፓስታ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 200,000 (ሁለት መቶ ሺ) ብር በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ያለባቸዉ ሲሆን የሞሉትን ጨረታ ሰነድ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ሰነድ ኦሪጅናል እና ፎቶ ኮፒ እንዲሁም የስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በተለያዬ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. የጨረታ አሸናፊነቱ ከተረጋገጠ ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት የዋጋውን ውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ ዉል መፈረም ይኖርባቸዋል፡፡
6. ተጫራች በሚያቀርቡት ዋጋ የጨረታ መግቢያ ሰዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ማሻሻያ ማድረግ እና ራሳቸውን ከጨረታ ማግለል አይቻልም፡፡
7. በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡
8. በጨረታ ሰነዱ ላይ የተሰረዘ እና የተደለዘ ሆኖ ለመለየት የሚያስቸግር ዋጋ ተቀባይነት የለውም።
9. ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ገንዘብ ከአሸናፊ ተጫራቾች ጋር ውል እንደተፈጸመ ተመላሽ ይሆናል፡፡
10. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የጨረታ ማስታወቅያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሆኖ በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት 8፡30 ላይ ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
11. የጨረታ መክፈቻ ቀናት ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም በበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
12. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ - ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 12ኛ ፎቅ
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011-558-25-19
ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ አ.ማ
Tender details
- Deadline: 2026-11-25
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሆኖ በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-25 14:30
- Bid opening (note): በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሆኖ በ16ኛው ቀን በ8፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Geda Transport and Logistics S.C.
- Buyer's registered address: ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 12ኛ ፎቅ
- Bid bond: 200,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Nov 10, 2026)
- Posted at: 2026-11-10T12:35:41.000Z
- Source: Qelal Tenders